አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2015፣ NBC ETHIOPIA – በሩሲያ ሰሜናዊ ምዕራብ ቴቨር አካባቢ በመከስከስ የ10 መንገደኞችን ህይወት በቀጠፈው የግል ጄት ላይ የዋግነር ፓራሚሊታሪ ቡድን መሪ ዬቭጄኒ ፕሪጎዝሂን እንደሚገኝበት ተረጋግጧል።

የሩሲያ አየር ትራንስፖርት ኤጀንሲ መግለጫው እንዳሳስታወቀው በረራው የተካሄደው በተቀመጠው አሰራር ሲሆን የአየር ክልልን ለመጠቀም በተፈቀደለት መሰረት እንደሆነም ገልጿል ” ።
ኤጀንሲው መጀመሪያ ላይ ልዩ የኮሚሽን ምርመራ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን ከሞስኮ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ ይጓዝ በነበረው አውሮፕላን ውስጥ ሰባት ተሳፋሪዎች እና ሶስት የአውሮፕላኑ ሰራተኞች እንደነበሩ አመልክቷል።

በመቀጠልም ኮሚሽኑ በቦታው ምርመራ መጀመሩን እና “በአውሮፕላኑ ቴክኒካል ሁኔታ፤ በበረራ መንገድ ላይ ስለነበረው የአየር ሁኔታ እና የምድር ሬዲዮ መሳሪያዎች ላይ ተጨባጭ ቁሳቁሶችን” መሰብሰብ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በሃና ተሰማ
ምንጭ(አናዱሉ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












