አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – በሳዑዲ አረቢያና የመን ድንበር ላይ በድንበር ጠባቂዎች ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ የኢትዮጵያ መንግስት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሳዑዲ አረቢያ በድንበር ጠባቂዎች ግድያ ተፈጽሟል የሚለውን የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት ላይ ማጣሪያ እየተደረገበት መሆኑን እና ማጣሪያው ተጠናቆ ግልጽ እስኪደረግም አላስፈላጊ መላምቶችን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።
በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ክትትል እንደሚደረግበትም ነው ያመላከተ ሲሆን ሁለቱ ሀገራትም መሰል አሰቃቂ ድርጊቶችን ያወግዛሉ በማለት ገልጾ፤ ሀገራቱ ረጅም ጊዜ የዘለቀውን ወዳጅነት እንዳላቸው ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውሷል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












