አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን የሚያካሂዱ እንዲሆኑ ለማስቻል የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ አዋጅ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ በመሆን በሚኒስትሮች ምክርቤት መፅደቁ ይታወሳል ።
ዪኒቨርስቲውም ራስ ገዝ ለመሆን ያለፈባቸው መንገዶች ፣የተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ ሊተገገበራቸው ያቀዳቸው ተግባራትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃንና ለዩኒቨርስቲው ሃላፊዎች መግለጫ ተሰጥቷል ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና ዩኒቨርስቲው ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ፣ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን ተግባራዊ እንዲያደርግ እና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንዲሆን ያስችላቸዋል ብለዋል።
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












