አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – ኒውካስትል ዩናይትድ የ18 ዓመቱን የቼልሲ ተከላካይ ሊዊስ ሃልን በውሰት ውል አስፈርሟል፡፡

የ21 ዓመቱ እንግሊዛዊ ለቼልሲ የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን በህዳር ወር በኒውካስትል በተሸነፉበት ግጥሚያ ያደረገ ሲሆን
በሚሰለፍበት ቦታ ላይ ክለቡ በርካታ አማራጭ ተጨዋቾችን በስብስብቡ ውስጥ በመያዙና በቂ የመሰለፍ ዕድልን ባለማግኘቱ ወደ ኒውካስትል አቅንቷል፡፡
ከልጅነቱ ጀምሮ የኒውካስትል ደጋፊ መሆኑን የሚገልፀው ተጨዋቹ ወደ ማግባይሶች በማምራቱ ኩራት እንደሚሰማው ተናግሯል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












