አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16/2015 ፣ NBC ETHIOPIA -የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ከ15ኛው BRICS የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በኦሮ ታምቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል ። የቻይናውን መሪ በጆሃንስበርግ ከሚካሄደው የ BRICS ጉባኤ በፊት በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።
ብሪክስ ብራዚልን፣ ሩሲያን፣ ህንድን፣ ቻይናን እና ደቡብ አፍሪካን የሚያጠቃልል የታዳጊ ኢኮኖሚዎች ስብስብ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ አንድ አራተኛውን ይይዛል፡፡ ከዓለም አቀፍ ንግድ አምስተኛውን የሚሸፍን ሲሆን ከ 40% በላይ የአለም ህዝብ መኖሪያን ይሸፍናል።
“ደቡብ አፍሪካ ከቻይና የእድገት ጎዳና ብዙ መማር አለባት” ከሌሎች ስኬቶች መካከል ቻይና በ40 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ወደ 800 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ከድህነት አውጥታለች ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
ራማፎሳ እንዳሉት ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የልማት አጋሮች እንደመሆናቸው ንግድ እና ኢንቨስትመንት የህዝቦቻቸውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ግንባር ቀደሞቹ እንደሆኑ የጋራ መግባባት ሲፈጥሩ ቆይተዋል።

በተጨማሪም የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ እና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጨምሮ ራማፎሳ ሌሎች በርካታ መሪዎችን በሚያስተናግድበት የ BRICS ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ።
በጉባኤው ላይ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ከ30 የሚበልጡ የሀገር መሪዎች እና መንግስታት ይገኛሉ።
በዩክሬን ተፈጽሟል በተባሉ የጦር ወንጀሎች ምክንያት አለም አቀፍ የእስር ማዘዣ የተጣለባቸው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በስብሰባው ላይ አይገኙም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ይወክላሉ ተብሏል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(አናዶሉ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/