አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA- ከተጀመረ 77ኛ ሳምንት በሆነው በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ብዙ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡

የዩክሬን ሀይሎች በዚህ ሳምንት አዲስ ወታደራዊ ድል ተቀናጅተናል እያሉ መሆኑም ታውቋል ፡፡
በተጨማም ወታደሮቿን በዲኒፕሮ ወንዝ ግራ መስመር በማሳለፍ በደቡብ ምስራቃዊ ግንባር አዲስ ጥቃት መጀመሯን ዩክሬን ገልፃለች ፡፡
በሌላ በኩል ግን በሰኔ ወር የካኮቭካ ግድብ ከተመታ በኋላ በጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የማይቻል አድርጎታል ተብሏል።
የዩክሬን ሀይሎች የመልሶ ማጥቃት ዘመቻቸውን ከጀመሩ ከ10 ሳምንታት በኋላ ተጨማሪ ግዛቶችን መያዛቸውን አስታውቀዋል። ዘገባው የአልጀዚራ ነው ፡፡
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc-












