
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA- በ2015 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት ከምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ102 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ግዥና ደንበኞች አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ አቶ ምኒልክ ጌታሁን እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ ፣ለሱዳንና ለኬንያ የኤሌክትሪክ የኃይል ትሸጣለች። ከዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከ 102 ሚሊዮን በላይ ዶላር አግኝታለች።
ሥራ አስኪያጁ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለጎረቤት ሀገራት ከሚቀርብ የኤሌክትሪክ ኃይል ከ143 ሚሊዮን በላይ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማግኘት የተቻለው 102 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ብለዋል።
እንደ ሥራ አሥኪያጁ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል በፍላጎት ልክ ሃይልን እያመረተ ነው። በ2015 በጀት ዓመትም 17ሺ 414 በላይ ጌጋዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ ኃይል አምርቶ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ማለታችውን ኢፕድ በዘገባው ገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












