አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA -በፓኪስታን ሁለት ግለሰቦች ቅዱስ ቁርዓንን አቃለዋል በሚል በሺዎች የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በምስራቃዊቷ ፑንጃብ ግዛት ጃራንዋላ ከተማ አብያተ ክርስቲያናትን በማቃጠል ጥቃት ፈፅመዋል።

በጥቃቱም የክርስቲያኖች መኖሪያ ቤቶች እና አራት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም ከአብያተ ክርስቲያናቱ ጋር የተያያዙ 12 የሚሆኑ ህንጻዎች ተጎድተዋል ።
በፓኪስታን የእስልምና እምነትን ማቃለልምና ማንቋሸሽ በሞት ያስቀጣል።
ምንም እንኳን ፍርድ ቤቶች የሞት ቅጣትን ተግባራዊ ባያደርጉም ከዚህ በፊት እምነቱን አራክሰዋል በሚል ብዙዎች ለደቦ የሞት ፍርድ መዳረጋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












