አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10/2015፣ NBC ETHIOPIA – ቫይታሚን_ዲ ከተለያዩ የምግብ ዓይነቶች የሚገኝ እንዲሁም በፀሐይ ብርሃን አማካኝነት ቆዳ ላይ የሚመረት የቫይታሚን ዓይነት ነው።

-ቫይታሚን ዲ ካልሲየም የሚባለውን ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም እንዲገባ ይረዳል።
-በተጨማሪም ለጡንቻ ስራ፣ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጎልበት እና የደም ስር በሽታዎችን ለመከላከል ሊረዳ ይችላል።
????ከፍተኛ_ቫይታሚን_ዲ_ያላቸው_ምግቦች

– ወተትና የወተት ተዋፅዖች
– የብርቱካን ጭማቂ
– ሳልሞን
– የታሸገ ቱና ዓሳ
– የዓሳ ዘይት (Cod liver oil)
– ጥራ ጥሬ እህሎች
????የቫይታሚን_ዲ_እጥረት_ምክንያቶች

– በቂ ቫይታሚን ዲ ከምግብ አለማግኘት
– በቂ የፀሐይ ብርሃን አለማግኘት
– በአንጀት በሽታዎች (ቫይታሚን ዲ ከአንጀት ወደ ደም በትክክል እንዳይገባ ስለሚያደርጉ)
– በኩላሊትና ጉበት በሽታዎች (ቫይታሚን ዲ በትክክል እንዳይመረት ስለሚያደርጉ)
????በቫይታሚን_ዲ_እጥረት_የሚመጡ_ችግሮች

– የአጥንት ጥንካሬ ማጣት እና በቀላል አደጋ የሚመጣ የአጥንት ስብራት
– የጡንቻ መዛል ይህንን ተከትሎ የሚመጣ የመውደቅ አደጋ
– በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ
– ለደም ስር በሽታዎች መጋለጥ
????የቫይታሚን_ዲ_እጥረት_እንዴት_ይታወቃል?

-የቫይታሚን ዲ መጠን በደም ምርመራ የሚታወቅ ሲሆን በውጤቱም መሰረት በ4 ይከፈላል።
– በቂ ከሆነ 30 ng/mL በላይ
– በቂ ያልሆ ከ 20 እስከ 30 ng/mL
– መጠነኛ እጥረት ከ12 – 20 ng/mL
– ከፍተኛ እጥረት ከ 12 ng/mL በታች
– ከልክ ያለፈ (መርዛማ ደረጃ) : ከ 100 ng/mL በላይ
????የቫይታሚን_ዲ_ምርመራ_ለማን_ይታዘዛል?

– በቂ የፀሐይ ብርሃን ለማያገኙ
– የአንጀት በሽታ ላለባቸው
– የአጥንት መሳሳት ላለባቸው
– በቀላል አደጋ የአጥንት ስብራት ላጋጠማቸው
– የካልሲየም መጠን ዝቅተኛ ለሆነባቸው
????የቫይታሚን_ዲ_እጥረት_ህክምና

– የቫይታሚን እጥረት መኖሩ ሲረጋገጥ ትክክለኛውን የቫይታሚን_ዲ ዓይነትና መጠን በሃኪም ትዕዛዝ መሰረት መውሰድ ያስፈልጋል።
– ከፍተኛ እጥረት ካለ በሳምንት አንድ ጊዜ 50,000 IU መጠን ያለው የሚዋጥ ቫይታሚን ዲ ለ2 ወር ከዛ በኋላ ደግሞ በየቀኑ ከ 800 – 1000 IU እንዲወሰድ ይመከራል።
– መጠነኛ እጥረት ካለ በየቀኑ ከ 800 to 1000 IU መጠን ያለው የሚዋጥ ቫይታሚን ዲ ይመከራል።
– በቂ ካልሆነ: በየቀኑ ከ 600 to 800 IU መጠን ያለው የሚዋጥ ቫይታሚን ዲ ይመከራል።
– ልጆች ላይ ቫይታሚን ዲ ከ 20 ng/mL በታች ከሆነ: ብዙ ጊዜ ከ 1000 to 2000 IU መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ ከ2 እስከ 3 ወራት እንዲወሰዱ ይመከራል።
– በተጨማሪም ቫይታሚን ዲ ሲወሰድ 1000mg መጠን ያለው ካልሲየም በየቀኑ እንዲወሰድ ይመከራል።
????የቫይታሚን_ዲ_የክትትል_ምርመራ

– መድሃኒት ከተጀመረ ከ 3 ወር በኋላ እና እንደአስፈላጊነቱ ቫይታሚን ዲ በደም በየጊዜው መመርመር ያስፈልጋል።
????የቫይታሚን_ዲ_መድሃኒት_የጎንዮሽ_ጉዳት

– ብዙ ጊዜ ተጨማሪ ቫይታማን ዲ ያለው መድብለ ቫይታሚን (multivitamin) ሲወሰድና ያለክትትል ቫይታሚን ዲ ለረጅም ጊዜ ሲወሰድ የቫይታሚን ዲ መጠን ከ 100 ng/mL ሊያልፍና የጎንዮሽ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል።
– የቫይታሚን ዲ ከመጠን ማለፍ የካልሲየም መጠንን በመጨመር የኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
???? የቫይታሚን_ዲ_እጥረትን_መከላከል

– የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዳይከሰት ከ 600 – 800 IU መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ በየቀኑ እንዲወሰድ ይመከራል።
– ቫይታሚን ዲ ከፀሐይ ማግኘት ይቻላል ነገር ግን ለብዙ ጊዜ ለፀሐይ ጨረር መጋለጥ የቆዳ መቃጠል (“Sunburn”) እና የቆዳ ካንሰር ተጋላጭነትን ሊጨምር ይችላል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc