አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10/2015፣ NBC ETHIOPIA -በሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በተቀሰቀሰው ግጭት በትንሹ 27 ሰዎች መሞታቸውን ተገለፀ።

የሊቢያ መንግስት የድንገተኛ ህክምና እና የድጋፍ ማእከል እንዳስታወቀው በትሪፖሊ 27 ሰዎች ሲሞቱ ፤ 106 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ታውቋል።
“የማዕከሉ ሰራተኞች ግጭቱ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች 234 አባወራዎች ተፈናቅለዋል” ብሏል።
ግጭቱ የተቀሰቀሰው የ444ኛ ብርጌድ አዛዥ ማህሙድ ሃምዛ በልዩ መከላከያ ኃይል በትሪፖሊ ሚቲጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከታሰረ በኋላ ነው።
ከሰኞ ምሽት ጀምሮ በሊቢያ ዋና ከተማ ከፕሬዚዳንቱ ምክር ቤት ጋር በተገናኘ በልዩ የመከላከያ ኃይል እና በብሔራዊ አንድነት መንግሥት 444ኛ ብርጌድ እና በታጠቁ ኃይሎች መካከል ግጭት እየተካሄደ እንደሚገኝ አናዶሉ ዘግቧል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc











