
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 08/2015፣ NBC ETHIOPIA -ጉባኤው የሚከናወነው “የአፍሪካን የአካባቢ ችግሮች ለመፍታታት ዕድሎችን መጠቀም፣ ትብብርን ማጎልበት” በሚል መሪ ሀሳብ መሆኑም ታውቋል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳንዶካን ደበበ፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የአካባቢ ጥበቃ የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም የዘርፉ የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ በሰዎች ላይ እያደረሰ ያለው ተፅዕኖን በሚመለከተ በሚቀርቡ ሪፖርቶች፣ እያጋጠሙ በሚገኙ ችግሮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል። ጉባኤው እስከ ነሐሴ 12/2015 ዓ.ም እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc