
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 08/2015፣ NBC ETHIOPIA- በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን ላይ የቆዩቱን ሞሐመድ ባዙምን በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ያስወገዳቸው የኒጀር ወታደራዊ ቡድን ፕሬዝዳንቱን በከባድ የሀገር ክህደት ሊከሳቸው መሆኑ ታውቋል።
መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው የኒጀር ወታደራዊ ቡድን ፕሬዝዳንት ባዙምን “በሀገር ክህደትና የሀገሪቱን ደህንነት ለአደጋ አሳልፎ በመስጠት በሚል ነው የከሰሳቸው ።
የወታደራዊ ቡድኑ ቃል አቀባይ ኮሎኔል አማዱ አብደራማኔ፣ ከሥልጣን የወረዱትን ፕሬዝዳንት ባዙም አድርገውታል ለተባሉ ስህተቶች ማስረጃዎችን እያሰባሰበባቸው መሆኑን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው መግለጫ አንብበዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc











