አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5 2015| NBC ETHIOPIA – በአውሎ ንፋስ ምክንያት የተቀሰቀሰው የከፋ የሰደድ እሳት በሃዋይ ማዊ ደሴት ላይ የምትገኘውን ታሪካዊቷ ላሃይና ከተማን አወደማት።

የማዊ የጤና ማዕከላት የእሳት ቃጠሎ ጉዳት በደረሰባቸውና በጭስ በታፈኑ ህመምተኞች መጨናነቃቸው ተነግሯል።
የግዛቲቷ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ብሪያን ሻትዝ ላሃይና “ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድማለች” በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መፃፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የእሳት አደጋ ሰራተኞች አሁንም እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ እንደሆነና የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪዎች ነፍስ አድን ሰራተኞች በህይወት ያሉትን በመፈለግ ላይ መሆናቸውን ብሪያን ሻትዝ ተናግረዋል።

በሰደድ እሳት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 53 ከፍ ማለቱን እና 1,000 ሰዎች በማዊ ደሴት ጠፍተዋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ወደ 2 ሺህ 100 የሚሆኑ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን እና በማዊ ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን
በአሁኑ ወቅት በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጹትባለስልጣናቱ የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc