አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5 2015| NBC ETHIOPIA – ወደ ኒጀር ጦር ለመላክ የተስማሙት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በአስፈላጊው ጊዜ የሚዘምት ጦር ለማቀናጀት መነጋገራቸውን የአይቮሪ ኮስት ፕሬዝደንት ገለፁ።

ኤኮዋስ የተሰኘው ቀጣናዊ ድርጅት አባላት የሆኑት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ስብሰባቸውን ሲያጠናቅቁ “በተጠንቀቅ የሚጠብቅ” ጦር ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
የአይቮሪ ኮስቱ መሪ አላሳኔ ኦዋታራ ፤ ከኤኮዋስ ስብሰባ በኋላ ከዚህ ቀድም ይህ ቀጣናዊ ድርጅት በአፍሪካ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለማስፈን ተሰማርቶ እንደነበር አውስተዋል።
ዛሬ ተመሳሳይ ነገር ኒጀር ውስጥ ገጥሞናል እኔ መናገር የምፈልገው ኤኮዋስ ይህንን እንደማይፈቅድ ነው፡፡ የአይቮሪ ኮስቱ ፕሬዝደንት እንደሚሉት ሀገራቸው ከ850 እስከ 1100 የሚሆን ጦር እንደምታዋጥጣ፤ ናይጄሪያ እና ቤኒንም እንዲሁ ወታደሮች እንደሚያዋጡ ገልፀዋል።

ይህ በተንጠቀቅ ይጠብቃል የተባለው ጦር ምን ዓይነት መልክ እንደሚኖረውና ምን ዓይነት ተግባር እንደሚፈፅም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጠበዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ዋን ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የቀድሞው ፕሬዝደንት ባዙም እና ቤተሰቦቻቸው “አስከፊ በሆነ ሁኔታ” ውስጥ በመሆናቸው ስጋታቸውን ገልፀዋል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












