
የተመድ የምዕራብ አፍሪካ እና የሳህል ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ሊዮናርዶ ሳንቶስ ሲማኦ “በአሁኑ ወቅት እየተፈጠረ ያለው ቀውስ መፍትሄ ካልተበጀለት በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይሄዳል ሲሉ ገልፀዋል ። “በተጨማሪም 4.3 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ በሚፈልጉበት ሀገር ውስጥ በህዝቡ ህይወት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል ማለታቸውን አናዱሉ ዘግቧል። አክለውም የመንግስታቱ ድርጅት እስካሁን በድርድር ላይ ባይሆንም በሀገሪቱ ያለውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ ሙሉ በሙሉ እየደገፈ ነው ብለዋል።
![]()
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ሀላፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በርካታ የመንግስት አባላት መታሰራቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸውም ምክትል ቃል አቀባዩ ፋርሃን ሃክ ተናግረዋል።ጉቴሬዝ የኒጀር ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ግዴታዎችን በጥብቅ መከተል እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በፍጥነት ወደነበረበት ለመመለስ በአስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

መሃመድ ባዙም እ.ኤ.አ. በ 1960 ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች በኋላ በኒጀር የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው ።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












