
ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር በሰጡት መግለጫ ባዙም በኒጀር ብቻ ሳይሆን በሰፊው የምዕራብ አፍሪካ አካባቢ ፀጥታን በማስፈን ረገድ የተጫወተውን ሚና አድንቀዋል።”ጸሐፊ ብሊንከን አሜሪካ በኒጀር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ለመመለስና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማምጣት ጥረቷን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ብሊንከን ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ማሃማዱ ኢሱፉ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው ባዙም “በእስር ላይ እንደሚገኝ እና በኒጀር ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለማረጋገጥ የሚደረገው ድርድር አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መውደቁ በጣም አሳሳቢ ነው ማለታቸውን ሚለር ተናግረዋል ።

ብሊንከን ኢሱፉን “በሲቪል የሚመራውን እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን መንግስት በመደገፍ ሁኔታውን ለመፍታት ጥረታቸውን እንዲቀጥል” ጠይቀዋል።
የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ከፈረንሳዩ አቻቸው ካትሪን ኮሎና ጋር የተለየ ውይይት ያደረጉ ሲሆን “በኒጀር እየተከሰቱ ባሉት ክስተቶች እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ባዙም መታሰር ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው” ሚለር ተናግረዋል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ራሳቸውን የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥበቃ ምክር ቤት (CNSP) ብለው የሚጠሩት ወታደሮች ባዙምን ከያዙ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በኒጀር የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፣ እርምጃውን የወሰዱት “የፀጥታው ሁኔታ እያሽቆለቆለ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ”በመኖሩ ነው ብለዋል።
ባዙም በ1960 ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች በኋላ በኒጀር የመጀመሪያው በዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር በ2021 የተመረጡ መሪ ናቸው።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት











