እቃዎቹ የተያዙት ከሐምሌ 14 እስከ 20/2015 በተደረገ ክትትል መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር የላቀ አፈጻጸም የተመዘገበ መሆኑን ያመለከተው ኮሚሽኑ በዚህም የኤርፖርት ፣ጅግጅጋ እና ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በቅደም ተከተላቸው 183 ሚሊዮን፣ 44 ሚሊዮን እና 28 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ መውሰዳቸውን አመልክቷል።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ሕብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 11 ግለሰቦች እና 4 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
የኮንትሮባንድ እና ህገ-ወጥ ንግድ ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ኮሚሽኑ ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩላቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ ማቅረቡን ኤዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












