
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ “የሽብር ሙከራው ተቀልብሷል” ብሏል። መከላከያ ሚኒስቴሩ ከሞስኮ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ኦዲንትሶቮ ከተማ አንድ ድሮን ተመትቶ መውደቁን እና ሌሎች ሁለት ድሮኖች አየር ላይ ከተመቱ በኋላ ሕንጻ ላይ ወድቀው ንብረት ማውደማቸውን አስታውቋል።
ዩክሬን ፈጽመዋላቸው ስለተባለው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የኪዬቭ ባለስልጣናት እስካሁን ያሉት ነገር የለም። ከዚህ ቀደምም በሩስያ ውስጥ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች የዩክሬን ባለስልጣናት ማረጋገጫ አይሰጡም።

በድሮን ጥቃቱ ምክንያት ከሞስኮ መሃል ከተማ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 28 ኪሎ ሜትር ላይ ርቆ የሚገኘው ቫኑኮቮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ስራውን እንዲያቆም ተደርጎ ነበር። ከዩክሬን ድንበር 500 ኪሎ ሜትሮችን ርቃ የምትገኘው ሞስኮ ይህ ነው የሚባል ጥቃት ተሰንዝሮባት አያውቅም። ይሁን እንጂ ከቅርብ ወራት ወዲህ ሩሲያ በመዲናዬ ሞስኮ ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እየተፈጸመ ነው ስትል ዩክሬንን ስትከስ መቆየቷ የሚታወስ ነው።ይሁን እንጂ ከቅርብ ወራት ወዲህ ሩሲያ በመዲናዬ ሞስኮ ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እየተፈጸመ ነው ስትል ዩክሬንን ስትከስ ቆይታለች።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት











