
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 19/2015 NBC Ethiopia- ግሪክ ከደቡብ ምስራቅ እስከ ሰሜን ምዕራብ ባሉት የሀገሪቱ ተቃራኒ በሆኑት በሮድስ እና ኮርፉ ደሴቶች ላይ የሚደርሰውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት ጥረቷን ቀጥላለች።
ሀገሪቱ በሶስተኛ የሙቀት ማዕበል ተይዛ ከ40C (104F) የሙቀት መጠን ከፍ በማለቱ ምክንያት መፈናቀሉ በሁለቱም ደሴቶች ቀጥሏል ሲል አናዱሉ ዘግቧል።
ከ 20,000 በላይ ሰዎች ፣ በተለይም ቱሪስቶች ፣ እስካሁን በደቡብ ምዕራብ ቱርኪ በሚገኘው ከሮድስ አካባቢ እንደተፈናቀሉ ታውቋል ።

የግሪክ የእሳት አደጋ አገልግሎት በትዊተር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው የኢቪያ ደሴት (Euboia) እና ማዕከላዊ አቲካን ጨምሮ በርካታ ክልሎች ከፍተኛ አደጋ ያጋጥማቸዋል ፣ ሌሎች ክልሎችም በተመሳሳይ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን አስታውቁዋል።
እሳቱ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ግሪክን ያወደመ ሲሆን ቱርክን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ግሪክ ላይ ያጋጠመውን ቤቶች እና ደኖችን ያቃጠለውን እሳት ለማጥፋት ድጋፍ አድርገዋል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebbok-https://www.facebook.com/ethiopiannbc












