
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 19/2015 NBC Ethiopia- በአልጄሪያ፣ ጣሊያን እና ግሪክ የሜዲትራኒያን ሰደድ እሳት መንደሮችን እና የመዝናኛ ቦታዎችን አደጋ ላይ በመጣል ከ 40 በላይ ሰዎች ሞተዋል ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል ።
አሁን ያለው ረዥም የሙቀት ሞገድ ምንም እረፍት አያሳይም – በአንዳንድ የግሪክ አካባቢዎች የሙቀት መጠኑ ከ 44C (111F) በላይ እንደሚጨምር ይጠበቃል። በሲሲሊ እና ፑግሊያ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰደዱ አድርጓል።

እስካሁን ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር በአልጄሪያ ሲሆን 34ቱ ተጎጂዎች 10 ወታደሮች በእሳት ነበልባል የተከበቡ ሲሆን ከአልጀርስ በስተምስራቅ በሚገኘው የባህር ዳርቻ ቤጃያ ግዛት ውስጥ በወጡበት ወቅት ነው። ቤጃያ በከፋ የተጠቁ አካባቢ ሲሆን ከሟቾቹ ውስጥ 23ቱን ይሸፍናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የአልጄሪያ ባለስልጣናት ከእሁድ ጀምሮ እሳቱ 80 በመቶው መጥፋቱን ገልፀው ነገር ግን ከፍተኛ የእሳት አደጋ መከላከያ ጥረቱ እንደቀጠለ ሲሆን ይህም ወደ 8,000 የሚጠጉ ሰራተኞችን፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ መኪናዎች እና አንዳንድ አውሮፕላኖችን ያካትታል።፡
በሰሜን አፍሪካ የተከሰተውን የሙቀት መጠን መጨመር ተከትሎ በአልጀሪያ የተከሰተው ከባድ ሰደድ እሳት ወደ ጎረቤት ቱኒዚያ ተዛምቷል።
ሁለት የድንበር መንገዶች እንዲዘጉም አስገድዷል 300 ሰዎች ከባሕር ዳርቻ ሜሎላ መንደር መውጣት ይኖርባቸዋል ተብሏል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc










