
አዲስ አበባ | ሐምሌ 11 2015 | NBC ETHIOPIA -በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር NBC Ethiopia የሚያዘጋጀው የሀሳብ መዋጮ ቶክ ሾው እሴትና የግለሰብ ሚና በሚል ውይይት አካሂዷል፡፡
ሀገራዊ አንድነትን፣ ህብረብሄራዊ ወንድማማችነትን፤ አብሮነትን መቻቻልን መከባበርንና አንዱ ለሌላው ማሰብን ለማሳደግ ብሎም የታሪክ ቁርሾን በማስተካከል ረገድ ሀገራዊ እሴቶች እጅግ ጠቀሜታ አንዳላቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በዛሬው የሀሳብ መዋጮ ዉይይትም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ምሁራን ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች አንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ኘሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ እሴትና የግለሰብ ሚናን ከማህበራዊ ስነልቦና አንጻር፤ አቶ እያሱ ባሬንቱ እሴትና የግልሰብ ሚናን ከፍልስፍና አንጻር ባህላዊ እሴቶች ለሀገር ያላቸውን ጠቀሜታ በጥናታዊ ፅሁፍ አስደግፈው አቅርበዋል፡፡


ባህላዊ እሴቶች የጌዜ እይታን ያዳብራሉ፣ በቂ ስራ ለመስራት ያግዛሉ ቁጠባን ያሳድጋሉ፣ ትምርትና እውቀት እንዲስፋፋ ይረዳሉ በተጨማሪም ስነምግባርና ፍታዊነትን ማስፈን አንደሚቸሉ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ጥናታቸውን ያቀረቡት ዶክተር ጥላሁን ተድላ ከፎክሎር አንጻር፣ ሀገራዊ እሱቶችን ከውስጥ ወደ ውጭ እንድንመለከት ያደርጉናል፣ የማህበረሰብና ግለሰብ ግንኘነት ያሻሽላሉ እንዲሁም የወል መግባቢያችን ማሳደግ እንደሚገባ አንስተው እሴቶች ለሀገር አንድነት፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብር ለመፍጠር ያላቸውን አስተዋፅኦ በመድረኩ ለተገኘው ታዳሚ አቅርበዋል ፡፡ በመጨረሻም ከመድረክ ለተነሳላቸው አስተያየትና ጥቄ ምሁራኑ መልስ ሰጥተዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia









