አዲስ አበባ ሐምሌ 8 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል።

በከተማ አቀፍም በጉለሌ የእጽዋት ማእከል የማስጀመሪያ ፕርግራም የተከናወነ ሲሆን በመድረኩ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን ፣የመከላከያ ሚኒሰትር አብርሃም በላይ፣የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የሀገራት አምባሳደሮች ፣የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።
በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ከከተማ ደረጃ ከ 4 ሚሊዮን በላይ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን በጉለሌ የእጽዋት ማእከል 50 ሺ ችግኞች የሚተከሉም ይሆናል ።

የዛሬው ቀን ኢትዮጵያን አረንጓዴ የምናለብስበት ታሪካዊ ቀን ነው ያሉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ አለም በአሁኑ ሰአት በአየር ንበረት ለውጥ ሳቢያ እየተፈተነችበት ባለችበት ወቅት ሀገራችን ይሄንን ለመቋቋም የችግኝ ተከላ ማከናወኗ ለቀሪው አለም ምሳሌ ያደርጋታልም ብለዋል።
ከንቲባ አደነች አቤቤ በበኩለቸው ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ለነገ ምግባችን መድሃኒታችንን የምናስቀምጥበት አለፍ ብሎም የአየር ለውጥን ተከትሎ የሚመጡ ፈተናዎችን ለመከላከል ያስችለናል ብለዋል።
በሰላማዊት ወልደገሪማ











