
አዲስ አበባ ሐምሌ 8 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- በተለያዩ የዓለማችን ከፍሎች በየዓመቱ እየተመዘገበ ያለው የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱ ታውቋል።
ጣልያን፣ ስፔን እና ግሪክ ባለፉት በርካታ ቀናት ከፍተኛ ሙቀት ከተመዘገበባቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ሆነዋል። የጣሊያን ጤና ሚኒስቴር መረጃ እንዳመለከተው ሮም፣ ቦሎኛ እና ፍሎረንስን ጨምሮ በ16 ከተሞች ከፍተኛ ሙቀት ይኖራቸዋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ በግሪክ የሙቀት መጠኑ 40 ዲግሪ ሴሊሺዬስ ደርሷል። በአቴንስ የቱሪዝስት መስህቦች አርብ እና ቅዳሜ ዝግ ተደርገውም ነበር። በስፔን ካናሪ ደሴቶች ደግሞ የተነሳው እሳት 4ሺህ ሰዎችን ያፈናቀለ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ 4ሺህ 500 ሄክታር መሬት ማውደሙ ተሰምቷል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia












