
አዲስ አበባ ሐምሌ 6 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከ43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ጎን ለጎን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብሽር ኦማር ጃማ ጋር በሁለትዮሽና አከባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ዛሬ በተጀመረው 43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሁለቱ አገሮች ወቅታዊ ወዳጅነትን በተመለከተ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሁሉም መስኮች የተሳሰሩ በመሆናቸው በጋራ ጉዳዬች ተባብረው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑክ ቡድን በ43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ምክርቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc