
አዲስ አበባ ሐምሌ 6 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- በኬንያ በትናንትናው ዕለት የግብር ጭማሪን አስመልክቶ በተቀሰቀሰው የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል።
ሰልፉ ወደ አለመረጋጋት መቀየሩን፣ ዘረፋና የመሰረተ ልማት ውድመት መድረሱን የአናዱሉ ዘገባ ያመለክታል ።
አንድ የኬንያ ጥምረት ፓርቲ መሪ እንዳሉት ፣ ተቃውሞው የተነሳው የኑሮ ውድነቱን እና በቅርቡ በነዳጅ ምርቶች ላይ የተጣለውን ቀረጥ ለማውገዝ ነው ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ያቃታቸው ዜጎች ብስጭታቸውን ለመግለፅና እና ለውጥን ለመጠየቅ ሰልፉን መቀላቀላቸው ታውቋል።
በሰላማዊ ሰልፈኞች እና በህግ አስከባሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በፍጥነት ተባብሶ በመላ ሀገሪቱ ግጭቶችን አስከትሏል ።
ፖሊስ በሰልፈኞቹ ላይ አስለቃሽ ጭስ በመተኮሱ ታቀወሞውን ይበልጥ ያልተረጋጋ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(አናዱሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc












