
አዲስ አበባ ሐምሌ 7፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- “ትምህርት ለትዉልድ” በሚል መሪ ቃል የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል

በትምህርት ቤቶች ላይ የሚሰራ ኢንቨስትመንት ተተኪ ትዉልድ ላይ መስራት እንደሆነ በማሰብ በከተማዋ በቂ መሠረተ ልማት ያልተሟላላቸዉን ትምህርት ቤቶች ማስተካከልና ማደሰ እንደሚገባ በንቅናቄዉ ተገልጿል።
ለዚህም በርካታዉን ድርሻ የሚወስደዉ ህብረተሰቡ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የልጆችን የነገ ህይወት ማሰብ የንቅናቄዉ ትልቁ አላማ ነዉ ተብሏል። በንቅናቄ መርሀ ግብሩ ሁሉም ክፍለከተሞች ሀላፊነት ወስደዉ እንዲሰሩ አደራ ተሰጥቷል።

በሀገራችን ለምንመኘዉ ለዉጥ ትልቁን ቦታ የሚይዘዉ ትምህርት በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ያሉት ከንቲባ አዳነች አበቤ በርካታ ስራዎች ይጠበቅብናል ሲሉም በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ ተናግረዋል።
በሊያ ክብሮም
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facbook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት











