
አዲስ አበባ |የካቲት 15 2015 | NBC ETHIOPIA- ቦኖሳይረስ የሚለውን ስያሜ ስንሰማ በቀጥታ ወደ ምናባችን የሚመጣው ምስል ሰዎች ለመመዝናናት እና ጥሩ የቤተሰብ ቆይታን ለማሳለፍ ከየአቅጣጫው ሲጎርፉ ይሳልብናል፡፡
ቦኖ ሳይረስ የአርጀንቲና ዋና ከተማ ስትሆን ከአላማችን ካሉ የመዝናኛ ስፍራዎች ርካሽ እና ብዙ የቱሪስት መስህቦች የሚጎረፉባት ውብ ከተማ ናት፡፡
በነገራችን ላይ ቦኖሳይረስ የሚለው ስያሜ ቅጥያ ስም ሲሆን ከላሪና ዲል ፕላታ በሰሜን አሜሪካ ማዕዘን መዳርሻ ከሚገኘው በተለምዶ የፕላታዋ ወንዝ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ነው ስያሜዋን ያገኘችው፡፡ በዚህም ቦነሳይረስ የፐላታዋ ወንዝ ንግስት በመባልም ትጠራለች፡፡
በዋና ከተማዋ 10 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች ይኖሩባታል፡፡ ቦኖ ሳይረስ በእውቅ የአውሮፓ አርክቴክቸሮች የስነ- ህንጻ ንድፍ ቅልቅል የተሰባጠረች አልፎም ተርፎ እጀግ ሳቢ የሆኑ ምግብና መጠጦች ሚገኙባት ፤ የእግር ኳስ ጨዋታም የሚዘወተርባት በአደባባዮቿ እና በጎዳናዎቿ ላይም የታንጎ ጭፈራን ብሎም የጭፍራ ሰልጣኞች ከአሰልጣኞቻው ጋር ድንቅ ትእሪት የሚያሳዩባት ከተማ ናት፡፡
የቦኖሳይረስ አመሰራረትም በ16ተኛው ከፍል ዘመን በወደብ ዳርቻ ላይ የከበሩ ማእድናት ንግድ ማእከል በነበረችበት ወቅት እንደነበር ታሪክ ያወሳናል፡፡
የሰሜን አሜሪካ ከተሞችን ሲጎበኙ ንጽህ የተፍጥሮ አየሮችን መኮምኮም የተለመደ ነው፡፡ የአየር ንብረቱ ሰፋፊ ጎዳናዎች እንዲሁም ቅንጡ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶም በሽበሽ ናቸው፡፡
ቦኖ ሳይረስ የተቀረጸችው በአውሮፓውያን ፈላሾች ነው፡፡ ለዚህም ነው የሰሜን አሜሪካዋ ፓሪስ ምትባለው፡፡
የስፔን ቀኝ ገዢዎች ችሎታና ጥበባቸውን በማሳረፍ በአለማችን አሉ ከሚባሉ ሃብታም ከተሞች ጎራ እንድትሰለፍ እረድተዋታል፡፡
ከተለያዩ ስፍራዎች የወጡ ስደተኞችም ኢልካሚንቶ በምትባለው በታዋቂዋ መዳረሻ ውብ ስፍራ ላይ ሲዘዋወሩ ማየት የተለመደ ነው፡፡
የላቦንቦኔራ ስቴዲየምም የእውቁ ማራዶና የእግር ማፍታቻ ስፍራ ናት፡፡
በጎዳናዎቿ ላይም ሽርሽር ካሉ የታንጎ ጭፍራን ከማየት ባሻገር ባህላዊ እና ዘመናዊ ሙዚቃዎችን ካጣጣሙ በኋላ በጎዳናው አቅራቢያ በምትገኘው የአንድ መቶ ሀምሳ እድሜ ባለጸጋ ወደ ሆነችው ካፌ ቶርቶኒ ጎራ ማለት የማይዘነጋ ነው፡፡
በጉብኝታችሁ ማገባደጃ ላይ በብዙ መስህቦቿ ከተማረካችሁ በኋላ በማያልቀው ወብ የከተማዎቾቿ መዳሻዎች ተማርካቹ አላልቅ እስኪላቹ ዞር ዞር ካላችሁ በኋላ አመሻሹን ለጎናችሁ እና ለእግራቹ ማሳረፊያ ቦታ ስታስቡ ቶርቶ ማድሬሮ ምሽታችሁን ያደምቅላችኋል፡፡
እናንተ ከልደከማችሁ በቀር ቦኖ ሳይርስ እንደሆን መሽቷል ደናደሩ አታቅም፡፡ እራታችሁን በብርሃን በደመቅው ማራኪ የብርሃን ምሽት ለጆሮ በሚያሳሱ ቆንጆ ቆንጆ ክላሲካሎች ታጀባቹ እስከ ጸሀይ ንጋት ድረስ ቆይታ ለማድርግ ደጆቿ ክፍት ናቸው፡፡
በፈርጥ በተንቆጠቆጡ ዘውዶች እና በማራኪ ጌጣጌጦች በሚያማምሩ ከነ- ህንጻዎቿ ፍቅር አለመነደፍ ከባድ ነው፡፡ ስለ ቦኖሳይረስ የሚሰማው እና የሚነገርላት ቃላቶች ሁሉ ምንም ግነት የሌለባቸው እውነታዎች ናቸው፡፡
በደቡብ አሜሪካ የምትገኘው አርጀንቲና ዋና ከተማ ናት፡፡ እጅግ ውብ እና ማራኪ የከተማ ውበትን የተላበሰች እና ለቱሪስቶችም ኪስ ሳትጎዳ የምታዝናና ከተማ እንደሆነች ይነገርላታል፡፡
በማህሌት ግርማ
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









