
አዲስ አበባ |የካቲት 14 2015 | NBC ETHIOPIA- በ36ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከ20 ሀገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ስኬታማ ዲፕሎማሲ ውይይት አድርገዋል አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ።
የአፍሪካ ሕብረት 42ኛ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ እና በ36ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በ36ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ዋዜማ የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ጉብኝት ዋና ዓላማ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጎለበትና ቀጣይ ግንኙነት ማሳለጥ፣ መተባበርና መደጋገፍን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን መከወን ያደረገ ነበር።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ያሏትን የዳበር ልምድ ያካፈለች ሲሆን የሳይንስ ሙዚየምን ጨምሮ ዘመኑን የዋጁ ለተቋማት መሰረት የጣሉ ስራዎችን ለፕሬዝንቱ ማስጎብኘት መቻሉ ተጠቅሷል።
የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንትም የኢትዮጵያን አሁናዊ ጉዞና እምርታ አድንቀው ፤የጠበቁት በጦርነቱ ምክንያት በርካታ ችግሮችን ቢሆንም ተቋማቱን ከጎበኙ በኋላ ግን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በተመለከተ ከፍተኛ አድናቆት የቸሩበት እንደነበር ተጠቅሷል።
በመሪዎቹ ያቀረቡት መክፈቻ ንግግር አዳዲስ ሀሳቦችና ለአፍሪካ የሚበጁ ብቻ ሳይሆን ያለፉ 60 ዓመታት የአፍሪካ የጋራ ትብብር ለማረጋጥ አባቶች ድርጅቱን ያቋቋሙበትን ምኞትና ራዕይ አድንቀዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ባለፉት 2 ዓመታት ያጋጠሟትን ችግሮቾ በኢትዮጵያዊ ጥበብና አርቆ አሳቢነት በኢትዮጵያ መፍትሔ መሻገር እንደሚቻል የቀዳማዊ ኃይለስላሴን ንግግር በማውሳት አንስተዋል።
አፍሪካ ችግሯን በራሷ መፍታት እንደምትችል ጠቅሰው፤ ይህም በግጭት ብቻ ሳይሆን አፍሪካን የሚፈታተኑ የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ የማያጋጥሙ ተግዳሮቶችን እንደአፍሪካ መፍታት እንደሚቻል የአረንጓዴ አሻራን ለአብነት ጠቅሰው ማብራራታቸውን አምባሳደር ታዬ አስረድተዋል።
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አስተዋጽ ትልቅ እንደሆነ መጥቀሳቸውንና በምግብ ራስን መቻል አቅም ርዕይ እያሳካች መሆኑና የአፍሪካ ችግር በአፍሪካ መፍታት አካል ሆኖ በተግባር መተርጎም እንዳለበት መጥቀሳቸው አስታውሰዋል።
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል ባለመሆኗ 60 በመቶ የአፍሪካ ጉዳይ እየቴየ ድምፅ አለመኖሯ የመብትና የፍትህ ጥያቄዋ አልተመለሰም፣ ይህይ እንዲታሰምም እንዲሁም በቡድን 7 እና በቡድንም 20 አባል እንድትሆን መጠየቋን አውስተዋል።
የዓለም አቀፍ ሚዲያ የተንሸዋረረ አተያይ የራሷን ሚዲያ ተቋሞ አቋቁማ የጎደፈ ገፅታዋን መመለስ እንዳለበታ መናገራቸውን ጠቅሰዋል።
ሌሎች የመልዕክታቸውም ዋና ዓላማም የፖን አፍሪካ ራዕይና ስሜት ያለበለት፤ የትብብርና የአንድነት ድምፅ እንደሆኑ ገልፀዋል።
ወደ 20 የአፍሪካ አገራት መሪዎቸ እና አንቶኒዮ ጉተሬዝን ጨምሮ ዓለምን አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች ማነጋገራቸው ተናግረዋል።
የሰሜኙ ጦርነት የተፈታበት መንገድ የተፈጠረውን የሰላም ቱርፋት የማሰለጥ፣ የመልስ ጎንባታ ማጠናከር ላይ ያጠነጠነ ውይይቶች ማድረጋቸውን ነበር።
የኢትዮ የአረንጓዴ አሻራና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የአካባቢው የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች እና የሰላም ችግሮቹ በጋራ የመፍታት ጉዳይ የሀሳብ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል ነው ያሉት።
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









