
አዲስ አበባ |የካቲት 15 2015 | NBC ETHIOPIA- ባሳለፍነዉ ሳምንት በመዲናችን ተደርጎ ከነበረዉ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ተከትሎ ኬንያ ያላትን የኢኮኖሚ ስጋት ገልፃለች።
በኬንያ በተለያየ ዘርፍ ዉስጥ ያሉ ነጋዴዎች ከአህጉሪቱ ጋር ለመገበያየት አስቸጋሪ ሰለሆነባቸዉ የሎጂስቲክስ እና የአስተዳደር እገዳዎች ስጋት ተናግረዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የሚሸፍነውን ጠንካራ ገበያ በመክፈት ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ያለውን ትልቅ አቅም ቢጠቅስም የአህጉራዊ የንግድ ልውውጥን በአግባቡ ለማቀላጠፍ አሁንም ብዙ ጉዳዮች አልተፈቱም።
የአበባ እና የአትክልትና ፍራፍሬ ገበሬዎችን የሚያገናኘው የኬንያ የአበባ ካዉንስል (KFC) እና ከተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተውጣጡ አምራቾችን የሚወክለው የኬንያ የአምራቾች ማህበር (KAM) የሎጂስቲክስ መሰናክሎች እና የድንበር ቁጥጥር ችግሮች አሁንም ላኪዎች ላይና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናዉ ላይ እንቅፋት እንደሆኑ ይናገራሉ።
የአበባ ምርት ዋና ስራ አስፈፃሚ ክሌመንት ቱሌዚ እንደተናገሩት ጥናቶች እንደሚያሳዩት ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ኮንጎ እና ቦትስዋናን ጨምሮ የመካከለኛው እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከኬንያ ምርት ለመግዛት መዘጋጀታቸውን ቢገልጹም፣ አምራቾች አሁንም መፍትሄ ባለማግኘታቸው ስጋት ላይ ናቸዉ ሲሉ ተናግረዋል።
ስራ አስፈፃሚዉ አክለዉ አብዛኛዎቹ ተግዳሮቶች ከሎጂስቲክስ ጋር የተያያዙ ናቸው። ግራ የሚያጋባ ነገር ነዉ ያለዉ ምርታችንን ወደ ኪንሻሳ ከመብረር ይልቅ ወደ አምስተርዳም ማብረር ቀላል ሆኖአል በጣም ዉድ ከመሆኑ የተነሳ። ምርቱን ወደ አምስተርዳም ማብረር የበለጠ ምክንያታዊ ነው ከአምስተርዳም ማንም የፈለገ ማግኘት ይችላል። ብዙ ሀገሮች ድበር ላይ ያሉ ችግሮችን አላስተካከሉም። ይህ ማለትም ላኪዎች ድንበሩ ላይ ከመድረሳቸዉ በፊት ስምምነቱ ላይ የሚያጋጥማቸው አይነት ችግር ይገጥማቸዋል ማለት ነዉ።
ችግሩ ይሄ ነዉ ላኪዎች ፓለቲካዊ በጎ ፈቃድ የሚያስፈልገዉና ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራዎች ያስፈልጋቸዋል።
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን በመመልከት ስምምነት አለን ማለት ይቻላል ነገር ግን በአፍሪካ ያሉ መንግስታት ድንበር ላይ ያሉ ችግሮችን በፍጥነት በማስማማት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።ያካልሆነ፣ ስምምነት አይጠቅመንም” ብለዋል ቱሌዚ።
ኬንያ ካሜሩንን፣ ግብፅን፣ ጋናን፣ ሩዋንዳን፣ ታንዛኒያን እና ቱኒዚያን ጨምሮ ምርቶቻቸዉን ለሌሎች ሀገራት ከሚያቀርቡ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት አካል ነች፣ ነገር ግን ከ2021 ጀምሮ በድንበር የሚሸጡ አብዛኛዎቹ ምርቶች ላይ የቀረጥ መቀነስ እርምጃን አሳይቷል።
በ 2030 አብዛኛው በአፍሪካ ውስጥ የሚሸጡ ምርቶች በድንበር ቦታዎች ላይ ቀረጥ የማይስቡ ከሆነ ነጋዴዎች ወደ ሌላ ሀገር መላክ ቀላል ይሆንላቸዋል ተብሏል።
የኬንያ አምራቾችም የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ለሀገር ውስጥ ንግዶች የሚሰጠውን ተስፋ አንስተዉ ነገር ግን እየታዩ ያሉ ተግዳሮቶች በመንግስታት ተገቢውን ትኩረት ይሻሉ ብለዋል።
በስምምነቱ መሰረት የንግድ ልውውጥን ለመጀመር በመንግስት የተከናወነውን ስራ እናደንቃለን። ስትራቴጂው የንግድ ስምምነቱን በፍጥነት ለመከታተል እና የኬንያ ንግድ እና ኢንቨስትመንት በአፍሪካ እንዲስፋፋ ለማድረግ ያለመ ነው ሲል የኬንያ የምርት ማህበር ተናግሯል።
ሆኖም ግን የንግድ ስምምነቱ ወደ ተግባር እንዲገባ ለማድረግ ብዙ ስራዎች መሰራት ያለባቸው እውነታዎች ናቸው። ከእነዚህ ተግዳሮቶች መካከል አንዳንዶቹ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ድርድርን ያካትታሉ፣ የጨርቃጨርቅ እና የአውቶሞቲቭ ሴክተር የመነሻ ህጎችን ጨምሮ ሲሉ የ ሥራ አስፈፃሚዉ አንቶኒ ምዋንጊ ተናግረዋል።
ይህም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የአፍሪካ መሪዎች ለ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲገናኙ ከመወያያ አጀንዳዎች አንዱ ነበር።









