
አዲስ አበባ |የካቲት 08 2015 | NBC ETHIOPIA-የዓለም ጤና ድርጅት ኢኳቶሪያል ጊኒ በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የማርቡርግ ቫይረስ በሽታ መከሰቱን አረጋግጡል፡
በበሽታው የሞቱት ዘጠኝ ሰዎች ኢኳቶሪያል ጊኒ ከካሜሩን ጋር በሚያዋስኑት ኪኢ-ንተም ግዛት በተፈፀመው የቀብር ሥነ ሥርዓትጋር የተያይዘ ነው።
የመካከለኛው አፍሪካ ትንሿ ሀገር ከ200 በላይ ሰዎችን ወደ ለይቶ ማቁያ ማስገባቷን እና ያልታወቀ የደም መፍሰስ ትኩሳት እንዳለ ከተገነዘበች በኋላ ባለፈው ሳምንት በኪዬ-ንተም ግዛት ውስጥ እንቅስቃሴን ገድባለች። ጎረቤት ካሜሩን የቫይረሱን ተላላፊነት ስጋት ስላደረባት በድንበሩ ላይ የእንቅስቃሴን ገድብ ጥላለች።
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ዶክተር ማትሺዲሶ ሞኢቲ በሰጡት መግለጫ ከዘጠኙ ሰዎች ሞት በተጨማሪ ኢኳቶሪያል ጊኒ በማርበርግ ቫይረስ የተጠረጠሩ 16 ሰዎች ትኩሳት፣ ድካም እና በደም የተበከለ ትውከት እና ተቅማጥ ምልክቶች ማሳየታቸውን አስታውቋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱን ለማከም የተፈቀዱ ክትባቶች ወይም የፀረ-ቫይረስ ሕክምናዎች የሉም። የማርበርግ ቫይረስ በሽታ እስከ 88 በመቶ የሚደርስ ሞት ሊያስከትል እንደሚችል ገልፃል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሚቶሃ ኦንዶ አየካባ ቫይረሱ የተቀሰቀሰው በኪ-ንተም ግዛት ንሶክ-ንሶሞ አውራጃ ውስጥ ካለው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የኢኳቶሪያል ጊኒ የአካባቢ ጤና ባለስልጣናት መጀመሪያ ላይ የካቲት 7 2023 እ.ኤ.አ ያልታወቀ ህመም ምልክቶች ሪፖርት እንደ ሄሞራጂክ(hemorrhagic) ትኩሳት፤ ድካም ሲደርሳቸው ናሙናዎችን በመውሰድ ወደ ሴኔጋል የሚገኝ ላቦራቶሪ እንደላኩ እና ከላብራቶሪ ውጤት አንዱ የማርበርግ ቫይረስ መኖሩ ማረጋገጡን የዓለም ጤና ድርጅት ተናግሯል።

የማርበርግ ቫይረስ (MVD) ቀደም ሲል ማርበርግ ሄሞራጂክ (Hemorrhagic) ትኩሳት ይባል ነበር፡፡ከኢቦላ ቫይረስ ጋር የአንድ ቤተሰብ አባል የሆነው ቫይረስ በሰዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የቫይረስ ሄመሬጂክ (Hemorrhagic) ትኩሳትን ያስከትላል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የማርበርግ የተከሰተው በ1967 በጀርመን ማርበርግ በምትባል ከተማ እና ሰርቢያ ነው። በሁለቱም ከተሞች በአንድ ጊዜ ወረርሽኝ ተከስቷል። ከኡጋንዳ ወደ ማርበርግ ለላቦራቶሪ ጥናት ከመጡ ዝንጀሮዎች የመጣ ሲሆን የላብራቶሪ ሰራተኞች ከዝንጀሮ ቁሳቁሶች (ደም፣ ቲሹዎች እና ሴሎች) ጋር በመስራታቸው ተበክለዋል። በዚህ ቫይረስ ጋር በተያያዙ 31 ጉዳዮች ሰባት ሰዎች ሞተዋል።
ከመጀመሪያዎቹ ወረርሽኞች በኋላ ቫይረሱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሪፖርት ተደርገዋል አብዛኛዎቹ ከአፍሪካ – ኡጋንዳ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና በጋና አሁን ላይ በጊኒ ቫይረሱ እንደታየ ጥናቶች አሳይተዋል።
ከ 2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ቫይረሱ ራሱን አዳብሮ ትኩሳት, ብርድ ብርድ ማለት, ራስ ምታት ምልክቶቹን ያሳያል በሽታው በድንገት ይጀምራል፡፡ምልክቶቹ ከታዩ በኋላ በአምስተኛው ቀን አካባቢ የማኩሎፓፓላር(maculopapular) ሽፍታ(ደረት፣ ጀርባ፣ ሆድ) ላይ በጣም ጎልቶ ይታያል። ማቅለሽለሽ, ማስታወክ, የደረት ሕመም, የጉሮሮ መቁሰል, የሆድ ህመም እና ተቅማጥ ሊታዩ ይችላሉ. ምልክቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከሩ ይሄዳሉ እና የጣፊያ እብጠት፣ ከባድ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የጉበት ድካም፣ ከፍተኛ የደም መፍሰስ እና የባለብዙ አካላት ስራን ማጣት ሊያጠቃልሉ ይችላሉ።
ሃና ተሰማ
ምንጭ (አልጀዚራ፤ የአለም ጤና ድርጅት፤ ቢቢሲ)
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት