
አዲስ አበባ |የካቲት 07 2015 | NBC ETHIOPIA-የአሜሪካ ተዋጊ ጀቶች በዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ የግዛት ክልል ላይ ሲበሩ የነበሩ ሁለት ግኡዝ ነገሮችን መትተው ጥለዋል፡፡ ምንም እንኳ ተመተው ስለ ወደቁት ስብስርባሪዎቹ የተሟሉ ተጨማሪ ትንተናዎች የሚያስፈልጉ ቢሆንም በህግ መወሰኛው ከፍተኛው የዴሞክራት አባልና መሪ ሻክ ሹመር ከቻይናው ፊኛ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
የሁለቱ አገር መሪዎች ይሁንታ ከሰጡ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ኤፍ 22 ተዋጊ ጀቶች በሰሜን አሜሪካ ላይ የነበሩትን ሁለት ጉእዝ ነገሮችን መተው ጥለዋል፡፡ በብሄራዊ የጸጥታ አማካሪው ማብራሪያ ከተሰጣቸው በኋላ ዴሞክራቱ ቻክ ሹመር ፊኛዎች መሆናቸውን እንዳመኑ ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ በቀደመው ሳምንት ተመቶ እንደወደቀው እንደ ቻይና ፊኛ ትልቅ አለመሆናቸውን ሹመር ሲገልጹ “ከዚህ ቀደም ከነበረው እጅግ ያነሱ ናቸው፡፡ አንደኛው በካናዳ አንደኛው አላስካ ላይ 40ሺ ጫማዎች ከፍታ ላይ ነበሩ፡፡ ለንግድ አውሮፕላኖች እጅግ አደገኛ መሆኑ ውሳኔው የተላለፈው ወዲያኑ ነበር፡፡” ብለዋል፡፡
በሁሮን ሃይቅ ጥቃት የመጀመርያው የሲዲዊንደር ሚሳኤል በዩኤስ ኤፍ-22 የጦር አውሮፕላን ኢላማውን ስቶ ባልታወቀ ቦታ ፈንድቷል ሲል የወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ሁለተኛው ሚሳኤል ኢላማውን መምታቱን ዘገባዎች ጠቁመዋል።እያንዳንዱ የሲዲዊንደር ሚሳኤል ከ400,000 ዶላር (330,000) በላይ ያወጣሉ።
ከመጀመሪያው ክስተት ጀምሮ፣ የአሜሪካ ተዋጊ ጄቶች ተጨማሪ ሶስት ከፍታ ያላቸውን ቁሶች በጥቂት ቀናት ውስጥ – በአላስካ፣ በካናዳ ዩኮን ግዛት እና በዩኤስ-ካናዳ ድንበር ላይ በሚገኘው ሁሮን ሃይቅ ላይ ተኩሰዋል ጥለዋል።
አሜሪካ ባለስልጣናት ከፍተኛ ከፍታ ያለው ፊኛ ከቻይና የመጣ እና ለክትትል ላይ ይውል እንደነበር ገልፀዋል ፣ ቻይና ግን የአየር ሁኔታን የሚቆጣጠር የአየር መርከብ ብቻ እንደነበር አሳውቃለች።
በአሜሪካ የአየር ክልል ሲንሳፈፉ ተገኙ በተባሉት ግዙፍ ፊኛዎች ምክንያት ውዝግብ ውስጥ የገቡት ቻይና እና አሜሪካ ሉዓላዊነትን በመጣስ እየተካሰሱ ነው።
ባለፉት ቀናት በአየር ክልሏ ውስጥ ያገኘቻቸውን የቻይና ፊኛዎች በተዋጊ አውሮፕላኖች መትታ መጣሏን ያሳወቀችው አሜሪካ፣ ወደ ቻይና ተመሳሳይ ፊኛዎችን አሰማርታ እንደነበር ቻይና ገለጸች።
ውዝግቡ እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት አሜሪካ ወደ ቻይና የአየር ክልል ከ10 ጊዜ በላይ ፊኛዎችን መላኳን ገልጿል።
ቻይና ለአየር ሁኔታ ጥናት ያሰማራሁት ፊኛ ነው ያለችው እና አሜሪካ ግን ለስለላ የተላከ ነው ብላ የጠረጠረችውን ፊኛ ከሳምንት በፊት መትታ መጣሏ ይታወሳል።
በጉዳዩ ዙሪያ ቻይና ለቀረበላት ጥያቄ በሰጠችው ምላሽ፣ አሜሪካ በተመሳሳይ የአየር ክልሏን የሚጥስ ድርጊት በተደጋጋሚ መፈጸሟን ገልጿለች።
“በአሜሪካ ጭምር የሚፈጸሙ በሕገ ወጥ ሁኔታ የሌሎች አገራትን የአየር ክልል የመጣስ ድርጊቶች ብዙም ያልተለመዱ አይደሉም” ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
“ባለፈው ዓመት ብቻ፣ የአሜሪካ ፊኛዎች ከቻይና ባለሥልጣናት ምንም አይነት ፈቃድ ሳያገኙ ከአስር ጊዜ በላይ በሕገ ወጥ መንገድ በቻይና የአየር ክልል ላይ ተንሳፈዋል።”
ይህ የአሜሪካ የአየር ክልል ጥሰት ባጋጠመበት ጊዜ ቻይና ምላሽ የሰጠችው “ኃላፊነት በተሞላበት እና ሙያዊ በሆነ መንገድ ነው” ብለዋል – ቃል አቀባዩ አሳውቀዋል።
በአሜሪካ የአየር ክልል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የቻይና ፊኛ ሲንሳፈፍ በመገኘቱ ምክንያት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊው አንቶኒ ብሊንክን ወደ ቻይና ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት ተሰርዟል። ክስተቱንም ብሊንከን “ተቀባይነት የሌለው እና ኃላፊነት የጎደለው” ብለውታል።
ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቶ የቆየ ሲሆን፣ ባለፉት ቀናትም ምንነታቸው ያልተለዩ ተጨማሪ በራሪ አካላትን አሜሪካ መትታ እንደጣላች አስታውቃለች።
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት
ሃና ተሰማ
ምንጭ
ቢቢሲ









