
ሃባብ ዘርፈ ብዙ የጥቅም ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥም ሰውነታችን ድርቀት እንዳይኖረው ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ይነግረናል፡፡ ሰውነታችን በተገቢው መንገድ አስፍላጊ ስራዎችን ለማከናወን እና በሕይወት ለመቆየት አስፈላጊውን ፈሳሽም ከሃባብ እናገኛለን፡፡
ሃባብ በሽታን ከመከላከል አንጻርም ግንባር ቅደም ተጠቃሽ ነው፡፡ ለአብይነት ብንጠቅስም ካንሰርን ይከላከላል፡፡ ለሰውነታችንም እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖችን፣ ማዕድናቶችን የያዘ ነው፡፡
በተጨማሪም የምግብ መፈጨት ስርአት እና የሰውነት ድርቀትን ለመከላከል እንደሚርዳም ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
ሀባብ ለአይናችን እይታም ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ በውስጡም ቫይታሚን ኤን ስለያዘ የሬቲና ቀለሞችን ለማዳበር ይረዳል፡፡ እንዲሁም የጡንቻ ህመምን ይቀንሳል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካደረግን በኋላ የሐብሐብ ጭማቂ መጠጣት የጡንቻ ህመምን ይከላከልልናል ይለናል ጥናቱ፡፡
ሐብሐብ መመገብ የልብ ህመምን እንደሚከላከል ጥናቱ አክሎ አስቀምጧዋል፡፡ በሀብሐብ ውስጥ ያሉ የልብ ጤናን ለመጠበቅ ከሚረዱ ቪታሚኖች እና ማዕድናት መሃከል ማግኒዚየም፣ፖታሲየም እና ቫይታሚን ኤ፣ቢ6 እና ሲ ይገኙብታል። እነዚህ መአድናትም ለጤና አስፍላጊ ከመሆናቸው ባሻገር ለልባችን አስፈላጊ ናቸው፡፡
ሐብሐብ ሲትሩሊን የተባለ አሚኖ አሲድ ሰለያዘ ፤በሰውነታችን ውስጥ የናይትሪክ ኦክሳይድ መጠንን እንዲጨምር ያደርጋል። በዚህም የደም ሥሮቻችን እንዲስፋፉ በመርዳት የደም ግፊትን ይቀንሳል፡፡
በተጨማሪም ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ አነስተኛ ካሎሪ በውስጡ ስለያዘ ጤናማ እና የተስተካከለ የሰውነት አቋም እንዲኖረን ከፈለግን ሃባብን ተመራጭ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
የሜታቦሊዝምን ስርአታችን በማፋጠን ስባችንን እንዲቅለጥ ከማድርግ አነጻርም ጉሉህ ሚና አለው፡፡ ሐብሐብ ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚን ኤ እና ሲ ለቆዳ ጤንነትም ጠቃሚ ናቸው። ቫይታሚን ሲ ስንመገብ ሰውነታችን ኮላጅን እንዲያመነጭ ይረዳል፡፡ ይህም ቆዳችን እንዲለሰልስ እና ጸጉራችን እንዲጠነክር ያደርጋል፡፡
ቫይታሚን ኤ የቆዳ ሴሎችን ለመፍጠር እና ለመጠገን ስለሚረዳ ለጤናማ ቆዳም እጅግ ጠቃሚ ነው ይለናል ጥናቱ ፡፡
ማህሌት ግርማ
ምንጭ (Health line)
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









