፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 22 2016| NBC ETHIOPIA- የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጁንግ ኡን በአንድ ጊዜ በርካታ ሮኬቶችን ማስወንጨፍ የሚችል እና አዲስ የመቆጣጠሪያ ስርዓት የተገጠመለት መሳሪያ ሲሞከር ማየታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን አስታወቁ፡፡
አዲስ የተሻሻለው ሮኬት በሁሉም መንገድ የተሳካ ጥቃት ማድረስ የሚችል ሁኖ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ኪም ጁንግ ኡን እንደዚህ ዓይነት መሳሪያዎች ለወታደራዊ አግልግልት የላቀ ድርሻ እንዳላቸውና ወደፊትም እየተሻሻሉ መሄድ እንደሚገባቸው ነው ያሳሰቡት፡፡
በኮሪያ ልሳነ ምድር የአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምድ እየተጠናከረ መምጣጡን ተከትሎ ፒዮንግያንግ ስጋት እንዳላት በተደጋጋሚ ምትገልጽ ሲሆን፤ ወታደራዊ አቅሟን ማሳደግ ትልቅ የቤት ስራዋ አድርጋለች ተብሏል፡፡
ላለፉት አስራ አንድ ቀናት አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጦር ልምምዳቸውን ማጠናቀቃቸውን ካስታወቁ በኋላ ነው ሰሜን ኮሪያ አዲስ የሮኬት ሙከራ ያደረገችው ሲል አር ቲ አስነብቧል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












