፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 22 2016| NBC ETHIOPIA- በሲዳማ ክልል መዲና ሀዋሳ መካሄድ በጀመረው መድረኩ ከ1800 በላይ የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የማህበረሰብ ወኪሎች፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች፣ የተቋማትና ማህበራት ተወካዮች እና የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነውበታል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር ሃገራዊ ምክክሩ ሊያመልጥ የማይገባ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን ገልፀው ለፍሬያማነቱ የሁሉም ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።

ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም በበኩላቸው የዓለም ሃያላን ሃገራት የሃያልነታቸው ምስጢር ችግራቸውን በምክክር መፍታታቸው ነው በማለት ህዝቡ ምክክሩን በባለቤትነት መንፈስ እንዲያካሂደው አደራ ብለዋል።

በዛሬው መርሃ ግብር በጠዋቱ ክፍለጊዜ ለተሳታፊዎች የአጀንዳ ልየታ ገለፃ የተደረገ ሲሆን ከከሰዓት ጀምሮ እስከ አርብ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ውይይት የሚደረግ ይሆናል።
ለሰባት ተከታታይ ቀናት በሚደረገው መርሃግብር ተወካዮቹ ከወከሉት ማህበረሰብ የሰበሰቧቸውን ሀገራዊ መግባባት ሊደረስባቸው ይገባል የሚሏቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረው ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚያስረክቡ ይሆናል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












