፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 17 2016| NBC ETHIOPIA- የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፌ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች አደጋው በደረሰበት ቦታ በመገኘት አጽናንተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት በሰውና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ አፈ ጉባኤውን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎችን በቦታው በመገኘት አጽናንተዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












