፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 18 2016| NBC ETHIOPIA-የምንጊዜም ተወዳጅ እና ትልቅ ተፅዕኖን መፍጠር ከቻሉ የካርቶን ፊልሞች መካከል ቀዳሚው ነው:: ዛሬ በዓለማችን የተከሰቱ አነጋጋሪ ሁነቶችን ከዓመታት በፊት ቀድሞ የተነበየ የፊልም ነብይ ነውም ይባልለታል-ዘ ሲምፕሰን
ዘ ሲምፕሰን በአሜሪካዊው ማቲ ኤብርሃም ሮኒነግ የፈጠራ ውጤት ሲሆን በፎክስ ብሮድካስቲነግ ካምፓኒ የሚተላለፍ አስቂኝ ተከታታይ የካርቶን ሲትኮም ነው፡፡ እንደ አውሮፓውያነኑ አቆጣጠር በ1987 ትሬሲ ኡልማን ሾው ላይ በአጭር ደቂቃ ይሄድ የነበረው ሲትኮም ተወዳጅነቱ ከፍ እያለ ሲመጣ በ1989 ግማሽ ሰአት ተመድቦለት መተላለፍ ጀመረ ፤በመቀጠልም በ 1990 በፎክስ ቴሌቪዥን ተላልፎ በርካቶች ተካታትለውታል፡፡

ይህ የካርቶን ፊልም በዋነኝነት 6 ገጸ ባህሪያት ያሉት ሲሆን ሌሎች በርካታ ገጸ ባህሪያት በየጊዜው ተካተው ተውነውበታል፤
በዋነኝነት የቤተሰብ አባላት ውስጥ ያለው ሁነት የሁሉንም ሰዎች የቤት ውስጥ ባህሪ እና አኗኗር በሚዳስስ መልኩ የሚቀርበው ይህ አስቂኝ የካርቶን ሲትኮም በጅማሮው ወቅት እምብዛም ተቀባይነት ባያገኝም ቀስ በቀስ ተወዳጅነቱ እየጨመረ መሄድ ችሏል፡፡
በ768 ትዕይንቶች በምዕራፎች ተከፋፍሎ የቀረበ ረዥሙ ተከታታይ የአሜሪካን ሲትኮም ነው፤
ሲምፕሰን ተከታታይ ሲትኮም ከማሳቅ፤ ከማዝናናት፤ እና የብዙ አሜሪካውያን የቤተሰብ ህይወት ከመግለጡ ባለፈ እስከዛሬ ድረስ የሚነገርላቸው በፊልሞቹ ሲኖች ላይ ገጸ ባሪያቱ የተናሩት ንግግር፤ የለበሱት አለባበስ ፤ የሚጠቀሙበት የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ጭምር በወቅቱ ያልነበሩ እና ከጊዜያት በኋላ ግን እውን ሆነው በርካቶችን ያስደነቁ ናቸው፤
በዚህም ሲምፕሰን ካርቶን ሲትኮም ሲነሳ በስፋት የሚነሳው ስለኢትዮጵያን ሁነት ጨምሮ በተለያየ ጊዜ በመጪው ጊዜ አለም ላይ ስለሚሆኑ ሁነቶች የተነበዩት ትዕይንቶች ናቸው፤
ይህ ሁነት ይበልጥ ሲምፕሰን እንዳይረሳ እና ሁልጊዜም ሁነቶች ሲፈጠሩ መለስ ተብሎ የድራማው ክፍሎችን እንዲቃኙ አድርጓል፡፡
ለዛሬም በዚሁ ተከታታይ የካርቶን ሲትኮም ላይ የታዩ ትዕይንቶች እና ከበርካታ አመታት በኋላ እውን መሆን ከቻሉ የድራማው ሲኖች መካከል ጥቂቶቹን እናስቃኛችኋልን፡፡

ሲምፕሰን ተከታታይ ካርቱን ሲትኮም በቴክኖሎጂው ረገድ በወቅቱ በእውናዊው አለም ያልነበሩ ነገር ግን በደራሲው ምናባዊ ፈጠራዎች አማካኝነት በሲትኮሙ ያሉ ገፀ ባህሪያት ሲጠቀሙባቸው ያየናቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች በርካታ ናቸው፡፡
እንደ ስማርት ሰአቶች፤ ቨርቹዋል ሪያሊቲ ቴክኖሎጂ እና በወቅቱ ይሆናሉ ተብለው የማይገመቱ እንደ ቪዲዮ ኮንፍረንስ ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ገጸ ባህሪያቱ በተለያዩ ክፍሎች ሲጠቀሙ ይታያል፡፡
ይህም ሁነት በወቅቱ እውን ሊሆን እንደማይችል የሚታሰብ እና ብዙዎቸን ፈገግ ያሰኘ አንዳንዱም ሰዎች እንደ ፊዝ ሲመለከቱት የቆዩት ሁነት ሲሆን በጊዜያት ሂደት እውን ሆኖ ሲመለከቱ ብዎች ሲትኮሙን መልሰው እንዲመለከቱ እና በሀሳቡ እንዲደነቁ ሆነዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2000 ላይ በተሰራው የሲምፕሰን ክፍል ሊዛ የተሰኘችው ገጸ ባህሪ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት በመሆን ትራምፕ የተሰኘ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ስለፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ስትናገር ይታያል፤አስቡት ይህ ሁነት የተፈጠረው በፈረንጆቹ 2000 ሲሆን በወቅቱ ትራምፕ የተሰኙ ግለሰብ ወደ አሜሪካን የፖለቲካ ስልጣን ያልመጡ ሰው ናቸው፡፡
በ2016 ዶናልድ ትራምፕ ለምርጫ ሲወዳደሩ እና ሲመረጡ ግን በርካቶች የሲምፕሰን ክፍል መለስ ብለው በመመልከት በትንበያውም ተደንቀዋል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 2014 በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው እና አስደንጋጭ ክስተት የሆነው የኢቦላ ወረርሺኝ በ1997 ሲምፕሰን ላይ ጭምጭምታው ታይቷል፡፡
የእናት ገፀ ባህሪ የምትጫወተው የካርቶን ካራክተር ልጇ ድባቴ ውስጥ ሲገባ ኪውሪየስ ጆርጅ ኤንድ ኮሮና ቫይረስ የሚል መፅፍ ስትሰጠው ይታያል፤ ይህ በሆነበት ከ17 አመታት በኋላ ታዲያ በአፍሪካዊቷ ኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ ተከስቶ ብዙ ጉዳትን አስከትሏል፤
ስለ ድምጻዊት ሌዲ ጋጋ የሱፐር ቦል ፐርፎርማንስ፤ ስለ ዲዝኒ መከፈል፤ ብራዚል ስለሚያጋጥማት የአለም ዋንጫ ሽንፈት፤ የ2016 የኢኮኖሚ ዘርፍ የኖቤል አሸናፊ ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሁነቶችን ፊልሙ ተተንብዩል፡፡
ታዲያ ሲምፐሰን በዚህ ሁሉ ክፍሉ ያልደረሰበት ያልዳሰሰው ርዕሰ ጉዳይ ባለመኖሩ ደራሲው በአንድ ወቅት ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፤ ተከታታይ ድራማ ያውም በዚሁ ሁሉ አመታት ያለፈ ሲትኮም ምንም ሁነት ሳይተነብይ ቢያልፍ ነበር ሊገርም የሚገባው የሚል ምላሽም ሰጥቷል፡፡
በፈረንጆቹ 2011 በሲምፕሰን 23ኛው ምዕራፍ ፉድ ዋይፍ በተሰኘ ርዕሰ ስለ ኢትዮጵያውያንም ሰርተዋል፡፡አስቂኝ ፤ አስገራሚ የሆነው ሲምፕሰን የካርቶን ተከታታይ ሲትኮም የምንጊዜም ተወዳጅ እና አይረሴ ከሆኑ በበርካታ ሚሊዮኖች ከታዩ እና የብዙዎች የልጅነት ትዝታም ሆነዋል፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












