Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

መጋኛ የቤል ፓልሲ (Bell’s Palsy)?

June 10, 2024
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 03 2016| NBC ETHIOPIA- የቤል ፓልሲ በተለምዶ ‹‹መጋኛ›› እየተባለ የሚጠራው በሽታ የፊት ጡንቻዎችን የሚቆጣጠረው ነርቭ (facial nerve) ጉዳት ሲደርሰበት ወይም ሙሉ በሙሉ መሥራት ሲያቆም የሚከሠት ነው፡፡ ይህ በሽታ የፊት ጡንቻዎች እንዲዳከሙ ወይም ሽባ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ፡፡

የቤል ፓልሲ በሽታ የያዛቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ይድናሉ፡፡ የተቀሩት ላይ ግን አንዳንድ ምልክቶች እስከ ዕድሜ  ልክ ይቀጥላሉ። የቤል ፓልሲ ምልክቶች ከአለብዎ ተገቢውን ሕክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይመከራል።

????ለየቤል ፓልሲ በሽታ የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምን ምን ናቸው?

የቤል ፓልሲ በሽታ ሁሉንም  የዕድሜ ክልል እና ሁለቱንም ፆታዎች በእኩልነት የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡

-የስኳር በሽታ

-እርግዝና

-ከዚህ በፊት በዚህ በሽታ የተጠቃ የቤተሰብ አባል ከአለ

-የደም ግፊት በሽታ

-አደጋ ከአጋጠመዎ

-አንዳንድ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች

-የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን  እንደ አጋላጭ ሁኔታዎች ይጠቀሳሉ፡፡

የቤል ፓልሲ የሚከሠተው የፊት ጡንቻዎችን የሚቆጣጠረው ነርቭ በሚያብጥ እና በሚቆጣበት ጊዜ ነው፡፡ ለዚህም የተለያዩ  ቫይረሶች እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል፤

-ምች የሚያመጣው ቫይረስ (herpes simplex virus)

-ኤች አይ ቪ ቫይረስ (HIV)

-አልማዝ ባለ ጭራ የሚያስከትለው (herpes zoster virus)

-ሳይቲሜጋሎ ቫይረስ  (cytomegalovirus)

-ኤፕስቲን ባር ቫይረስ (epstein bar virus) ይጠቀሳሉ፡፡

???? የቤል ፓልሲ ምልክቶች

የቤል ፓልሲ በሽታ በከፊል የፊት ጡንቻዎችን የሚያሰንፍ ሲሆን፤ ችግሩ የሚከተሉትን ምልክቶች በግማሽ የፊት ገጽታ ላይ ያስከተላል።

– የቅንድብ፣ የዐይን ሽፋን እና የአፍ ጥግ መውደቅ

-አንድ ዐይን ሙሉ በሙሉ የመዘጋት መደበኛውን ችሎታ ማጣት። ይህም የዐይን ንጣፍ (ኮርኒያ) እንዲደርቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡

-መሳቅ፣መኮሳተር ወዘተ ዓይነት ስሜቶችን በፊት መግለጽ አለመቻል፡፡

-የምራቅ እና የእንባ መጠን መቀነስ

– ራስ ምታት

 -የምራቅ መዝረብረብ

-ከፍ ያሉ ድምፆች በተጎዳው ጎን ያለው ጆሮ ላይ ምቾት መንሣት (dysacusis)

 -አንዳንድ ሰዎች ላይ በምላስ የፊተኛው ክፍል የጣዕም ስሜትን ማጣት

-በተጨማሪም በድንገት የሚከሠት ስለሆነ የጭንቀት እና የደንጋጤ ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡

የቤል ፓልሲ በሽታ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ በአንድ ወይም በሁለት ቀናት ውስጥ መታየት ሲጀምሩ  አብዛኛዎቹ  ሕመምተኞች በሦስት ሳምንታት ውስጥ መሻሻል ያሳያሉ፡፡ ሙሉ በሙሉ ለማገገም  ከሶስት እስከ  ስድስት ወር ሊቆይ ይችላል ፡፡

???? የቤልስ ፓልሲ ሕክምና

የቤል ፓልሲ በሽታ ፈውስ የለውም፡፡ ነገር ግን ሕክምናው በፍጥነት ለመዳን ይረዳል፡፡ በተለይም ሕክምናው በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የተጀመረ ከሆነ የበለጠ ውጤታማ ይሆናል። ሕክምናው የሚከተሉትን ክፍሎች ይይዛል።

???? የዐይን እንክብካቤ

ዐይንዎን መዝጋት ከአልቻሉ የዐይን ሕክምና ያስፈልግዎታል፡፡ ለዐይን ግልፅ የመከላከያ ሽፋን የሆነው ኮርኒያ ከመጠን በላይ ደረቅ ከሆነ ዘላቂ የሆነ የዐይን ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

ይህንንም ለመከላከል የዐይን እርጥበት እንዲኖር  ሰው ሠራሽ እንባ (የዐይን ጠብታ) መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ የዐይን ጠብታውን የእይታ መደብዘዝ እንዳያመጣ ማታ ላይ መጠቀም የተሻለ ነው። ቀን ላይ ዐይንዎን ከአቧራ እና የመሳሰሉት ለመጠበቅ መነጽር መጠቀም አለብዎት፡፡

???? በእንቅልፍ ሰዓትም የዐይን ሽፋን ማድረግ ተገቢ ነው።

???? መድኃኒቶች

-በቤል ፓልሲ በሽታ መያዝዎ በቶሎ ከታወቀ (ከመጀመሪያዎቹ ከ 2 እስከ 3 ቀናት ውስጥ) በስትሮይድስ (steroids) ለአንድ ሳምንት ያህል ይታከማሉ፡፡ ይህም መድኃኒት የነርቭ እብጠትን ሊቀንስ እና ሙሉ በሙሉ የመዳን ዕድልን ያሻሽላል ተብሎ ይታመናል።

-የፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች (ለምሳሌ  valacyclovir) አንዳንድ ጊዜ  ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ነገር ግን   እነዚህን  መድኃኒቶች  መጠቀም ተጨማሪ ጥቅም ማስገኘቱን ጥናቶች አላረጋገጡም፡፡

-የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶች

– አኩፓንቸር (Acupuncture)

-የኤሌክትሪክ ንዝረት ሕክምና (Electrical stimulation)

-አካላዊ ሕክምና (physical therapy)

???? ለቤል ፓልሲ ሕመም በቤት ውስጥ የሚደረግ እንክብካቤ

-የዐይን መሸፈኛ መጠቀም

-ለብ ባለ ውሃ የተነከረ ፎጣ በተጎዳው ፊት ላይ ማድረግ

-የተጎዳውን ፊት ማሸት ወይም ማሳጅ ማድረግ

-በብርጭቆ ለመጠጣት አስቸጋሪ ከሆነ በመምጠጫ (straw) መጠቀም

ShareTweetShare
Previous Post

የፕሪዝን ብሬክ አስገራሚ እውነታዎች

Next Post

የስፖንጅ ከተሞች

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
የስፖንጅ ከተሞች

የስፖንጅ ከተሞች

በናይጄሪያ የተፈጸመ ጥቃት 

በናይጄሪያ የተፈጸመ ጥቃት 

ኢትዮጵያ በብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

ኢትዮጵያ በብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?