፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 13 2016| NBC ETHIOPIA- “የኢትዮጵያ ሚዲያ ለኢትዮጵያውያን ውጤታማ ምክክር” በሚል ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሚዲያ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የሚመክር መድረክ አዘጋጅቷል።
ሚዲያዎች ስለምክክሩ በርካታ ዘገባዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን የገለፀው ኮሚሽኑ እልባት የሚሹ ክፍተቶች መኖራቸውን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በክልሎች የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በቂ የሚዲያ ሽፋን አለማግኘታቸው አንዱ ክፍተት ነው ተብሏል።
ለሃገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት የሚዲያው ዘርፍ የበለጠ እንዲሰራ ጥሪ ያቀረበው ኮሚሽኑ መጪዎቹ አስር ወራት የምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ በመሆናቸው ሚዲያው ለምክክሩ መሳካት እስካሁን ሲያከናውን ከነበረው በላይ እንደሚጠበቅበት ገልጿል።
ሃገር ወደአለመረጋጋት በምትገባበት ጊዜ ሚዲያ ሰላምን በማስፈን ረገድ ከፍተኛ ሃላፊነት እንዳለበት በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን 11 ሚዲያዎች ተመርጠው በእስካሁኑ ቆይታ ስለሃገራዊ ምክክሩ ሲያከንውኗቸው የነበሩ ተግባራት የተገመገመበት ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።
ስለምክክሩ በሚዲያ ህዝቡን ተደራሽ ለማድረግና ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ሲሰሩ የቆዩ ስራዎች ጥንካሬና ድክመት በመለየት በቀጣይ የሚኖረው ጉዞ ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያግዛል የተባለለት ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
በ-መቅደስ ደምስ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












