Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

ታይተው የማይጠገቡ የዓለማችን የተፈጥሮ መስህቦች

May 17, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ 

ዓለማችን በልዩ ልዩ የተፈጥሮ ሃብቶች የበለጸገች እና የታደለች ናት፡፡ ግዙፍ የበረዶ ግግሮች፣ አስደናቂ የመልካምድር አቀማመጥ፣ ጥቅጥቅ ደኖች፣ ፏፏቴዎች  እንዲሁም ሌሎች እጅግ አስደናቂ ያልተነገረላቸው ተፈጥሮችን ታድላለች።

ለዛሬ በዓለማችን እጅግ ውብ የሆኑ እና የተፈጥሮን እጽብ ድንቅነት ያስመሰከሩ የተፈጥሮ መስህቦችን በጥቂቱ እናስመልክታችሁ።

????የአማዞን ጥቅጥቅ ጫካ

ሰፊው እና ጥቅጥቁ የአማዞን ደን ብራዚል፣ፔሩ እና ኮሎምቢያን ጨምሮ ደቡብ አሜሪካ ይሸፈናል። አማዞን በዓለማችን ላይ ትልቁ ጥቅጥቅ ደን ሲሆን፣ ከ40,000 በላይ የእፅዋት ዝርያዎች 1,300 የወፍ ዝርያዎች ፣ከ 3,000 በላይ የዓሣ ዝርያዎች እንዲሁም ወደ 400 ቢሊዮን የሚጠጉ ዛፎች መገኛ ነው። ስፈራው እጅጉኑ ለአይን ማራኪ ከመሆኑ ባሻገር በውስጡ የሚገኙ ጠመዝማዛማ ወንዞች እና የከበቡት ድንቅ ተፈጥሮአዊ ስፍራዎች የጎብኚዎች ተመራጩ መዳረሻ አድርጎታል፡፡

ይህ ድንቅ የተፈጥሮ ደን ስድስት ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትርን እንደሚሸፍን የሚነገር ሲሆን፤ በምድር ላይ ከሚታወቁት  ዝርያዎች 10 በመቶ ያህሉን መያዙ ደግሞ ልዩ ያደርገዋል፡፡

????የካፖዶሺያ መልከአ ምድር

በቱርክ በማዕከላዊ አናቶሊያ የሚገኘው ይህ ስፈራ በተለየ የመሬት አቀማመጡ በልዩነት ይታወቃል። አስደናቂ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ያለው ስፈራው ከ60 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በማዕከላዊ አናቶሊያ ከተከሰተው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በኃላ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

በስፍራው መልከ ብዙ ታሪካዊ ቅርሶች እና ማራኪ ገጽታዎች ያሉት ሲሆን፤ ከመላው ዓለም በርካታ  ቱሪስቶች ይጎርፉበታል፡፡ የአየር ፊኛ ጉዞዎችም ቱሪስቶች ስፍራውን ከፍ ብለው ለመመልከት ተመራጩ ነው፡፡

ከአስደናቂ የመሬት ገጽታ በታች ተደብቀው የሚገኙ ‘ከመሬት በታች ያሉ ከተሞች’ ሌላኛው የቱሪስቶች መዳረሻ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በርካታ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናት ፤በቤተመቅደሶቹ መነኮሳት የተቀረጹ በርካታ ቅርሶች እና አስደናቂ የሆኑ ስዕላት ይገኛሉ።

እ.ኤ.አ በ2019 ብቻ 3.8 ሚሊዮን የውጭ ቱሪስቶች ወደዚህ ስፈራ አቅንተዋል።

????ዳንኪሲያ ላንድፎርም ፤ ቻይና

ዳንክሲያ ላንድፎርም በቻይና የሚገኝ የጂኦሎጂካል ፓርክ ሲሆን፤ በቀለማት ያሸበረቁ የተፈጥሮ ተራራ እና ቀይ የአሸዋ ድንጋይ የተከበበ ነው፡፡

የዳንክሲያ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተለያየ መጠንና ቅርጽ ባላቸው በርካታ ዋሻዎች የተሞላ ሲሆን፤ መቶ ሜትር ከፍታ ያላቸው በርካታ ቀይ ቋጥኞችን አቅፎ ይዟል፡፡

ስፍራው በቀይ የአሸዋ ድንጋይ መሸርሸር ምክንያት እንደተፈጠረ ይነገራል፡፡ መልክዓ ምድራዊ አወቃቀሩ ፣ ከቀስተደመናማ የስፍራው መልክ ጋር ተዳምሮ ስፈራውን ልዩ አድርጎታል። በርካቶች ዳንኪሲያ ላንድፎርምን ለመጎብኘት ወደ ስፍራው ያቀናሉ፡፡

????በጃፓን የሚገኙ የአራሺያማ የቀርከሃ ጫካዎች

ስፍራው ከጃፓኗ ኪዮቶ ወጣ ብሎ የሚገኝ ሲሆን፣ ረጃጅም የቀርከሀ ዛፎች እና ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች ይገኝበታል።

አራሺያማ የቀርከሃ ጫካዎች፣ በአለም ላይ በብዛት ፎቶግራፍ ከተነሱ ቦታዎች አንዱ ስለመሆኑ ይነገራል። ይህንን  አስደናቂ በቀርከሃ ዛፎች የተከበበ ስፍራ ለመመልከት በርካቶ በየዓመቱ ወደዚህ ስፈራ ያቀናሉ።

ይህ የቀርከሃ ጫካ በልዩነቱ የሚታወቀው የቀርከሃ ዝርያ የሚገኝበት ነው፡፡ ይህ የቀርከሃ ዝርያ እስከ 92 ጫማ ከፍታ ያለው እና እጅግ የሚያምር እይታን የተላበሰ ነው። የቀርከሃ ዛፉ የቦታው ተፈጥሯዊ ውበት በመሆኑ ተወዳጅ መዳረሻ እንዲሆን አስችሎታል። በጫካ ውስጥ እየተንጎራደዱ የእግር ጉዞ ለቱሪስቶች ልዩ ስሜት የሚፈጥር ነው፡፡

????በማሌዥያ ካሜሮን የሚገኙ አስገራሚ ተራሮች

በካሜሮን ከባህር ጠለል በላይ ከ2000 ሜትር በላይ ከፍታ ያላቸው ተራሮች የተፈጥሮን ውበት በሌላ መልክ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ናቸው፡፡ በማሌዥያ በፓሃንግ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ስፍራው፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የሻይ እርሻዎች ፣ የእንጆሪ እርሻዎች ፣ሸለቆዎች እንዲሁም ተራራማ ኮረብታዎች ይገኙበታል፡፡

አካባቢው ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ የተላበሰ ሲሆን፣ በፏፏቴዎች፣ በወንዞች፣ በሐይቆች፣ በዱር እንስሳት እና በልዩ ልዩ የተፈጥሮ ሽልማቶች የደመቀ ነው፡፡ የስፈራው አስደሳች መልክዓ ምድር  እና ቀዝቃዛ የአየር ጠባዩ ደግሞ የጎብኝዎች ተመራጭ ስፍራ አድርጎታል፡፡

በ-ሀይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Next Post

ለሞት ከሚዳርጉ ህመሞች 16 በመቶውን ድርሻ የሚይዙት ከፍተኛ የደም ግፊት የሚያስከትላቸው በሽታዎች ናቸው ተባለ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
ለሞት ከሚዳርጉ ህመሞች 16 በመቶውን ድርሻ የሚይዙት ከፍተኛ የደም ግፊት የሚያስከትላቸው በሽታዎች ናቸው ተባለ

ለሞት ከሚዳርጉ ህመሞች 16 በመቶውን ድርሻ የሚይዙት ከፍተኛ የደም ግፊት የሚያስከትላቸው በሽታዎች ናቸው ተባለ

የአምልኮ ስፍራ ጥቃት በፈረንሳይ

የአምልኮ ስፍራ ጥቃት በፈረንሳይ

የቻይና ማስጠንቀቂያ

የቻይና ማስጠንቀቂያ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?