፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 30፣ 2016| NBC ETHIOPIA-የአርሰናል አምበል ማርቲን ኦዲጋርድ የቡድን አጋሮቹ ለሀሪ ኬን ክብር እንዲሰጡ አሳስቧል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ነገ ምሽት ከ4፡00 ጀምሮ በሜዳው ከባየርን ሙኒክ ጋር ይጫወታል።
የጀርመኑ ክለብ በቡንደስሊጋው በዶርትመንድና ሀይደንሃይም ከደረሰበት ተከታታይ ሽንፈቶች ማግስት ነው ወደ እንግሊዝ ተጉዞ የሚኬል አርቴታን ቡድን የሚገጥመው።
ምንም እንኳ ቡድኑ ከቡንደስሊጋውና ዲ ኤፍ ቢ ፖካል ፉክክሩ ዉጭ መሆኑ የተረጋጋጠ ቢሆንም እንግሊዛዊው አጥቂ ሀሪ ኬን ግን በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 37 ጨዋታዎች 38 ጎሎችን በማስቆጠር በግሉ መልካም የውድድር ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል።
በሮበርት ሌቫንዶስኪ የተያዘውን የሊጉን የ42 ጎል ሪከረድ ለመጋራት ብሎም ለማሻሻል10 እና ከዚያ በላይ ጎሎች ይቀሩታል።
ኖርዌያዊው የአርሰናል አምበል ማርቲን ኦዲጋርድ ስለዚህ አስደናቂ አጥቂ ሲጠየቅ፣ “እርሱን ማክበር ይጠበቅብናል ብየ አስባለው፣ ነገር ግን ማንንም አንፈራም” ብሏል።
“ሀሪ ኬን ጥሩ ተጨዋች ነው፣ ለጥቂት ጊዜያት ቢሆንም ከእርሱ በተቃራኒ ሆኜ ተጨዋቻለሁ ሳጥን ውስጥ ሲገባ ያለውን የመጨረስ አቅምና የቅብብል ችሎታውንም እናውቃለን” ሲል አክሏል።
ይሁንና እርሱና ጓደኞቹ ትኩረታቸው ሊሆን የሚገባ፣ እራሳቸው ላይ ብሎም በቡድናቸው ውስጥ ያለው አቅም ላይ እንደሆነ አሳስቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












