፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 30፣ 2016| NBC ETHIOPIA- የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሩዋንዳ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ፡፡
-ከ900 በላይ ስታርት አፖች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ በሣይንስ ሙዚየም ተከፈተ።
-በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቱሪዝም መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎችን እና ተቋማትን ያሳተፈ የቱሪዝም ማስተዋወቅ ኩነት አደረገ።
-የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ የሚፈፀመው ስርቆት አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ተግዳሮት እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
-የከተማና መሰረት ልማት ሚኒስቴር ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የቢሮ ቁሳቁስ እና 11 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ።
-በቄለም ወለጋ ዞን ዳሌሰዲ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












