አዲስ አበባ | የካቲት 19፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የጤና ሚኒስቴር ከዩ ኤስ አይ ዲ፣ ዩኒሴፍ እና ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጀው 3ተኛው ሃገር አቀፍ የማህበራዊ እና ባህሪ ለውጥ ጉባዔ መክፈቻ መርሀ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው በማህበራዊ እና ባህሪ ላይ የተከናወኑ ጥናት እና ምርምሮች፣ የፈጠራ ስራዎች፣በዘርፋ የተሻለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሞያዎች እውቅና እና ምስጋና ሽልማትእንዲሁም ተሞክሮዎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

የማህበረሰብ ባህሪ ለውጥ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ የጀመረው ጉባዔው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 2ቀናት ይቆያል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በሀገር አቀፍ ደረጃ በማህበረሰቡ ዘንድ የባህሪ ለውጥ እንዲመጣ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መንገዶችን የጤና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራት ሲከናወን መቆየቱን በመግለጥ ተጨባጭ የሆኑ ለውጦች መምጣት መቻላቸውን ገልፀዋል።

“የኛ” የተሰኘ ፕሮጀክት በመንደፍ ድራማዎች፣ የምክክር መድረኮች እና ጭውውቶችን በማዘጋጀት ሴቶች የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ እና ሀሳባቸውን በነፃነት መወያየት እንዲችሉ ከ10 ዓመታት በላይ ሲሰራ መቆየቱን የገርል ኢፌክት ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ፋናዬ ገብረህይወት በመክፈቻ መርሀ-ግብሩ ተናግረዋል።
ከሱማሌላንድ፣ ኬንያ፣ ጋና፣ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ህንድ፣ካናዳ እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በመድረኩ ታድመዋል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












