አዲስ አበባ | ታህሳስ 26፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የገና እንዲሁም የጥምቀት በዓል በማስመልከት የማዘጋጃዊ ቤት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።

የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገበየው ካሳ በበዓላቱ የሀይል መቆራረጥ እንዳይከሰት ዝግጅት ማደረጉን ተናግረዋል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የቅድመ ክፍያ ደንበኞች በ8 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ገልፀዋል።
4ኪሎ፣ አያት፣ወሰን፣ ካሳንችስ፣ልደታ፣ቃሊቲ፣ ለቡ እንዲሁም አየር ጤና ደንበኞች አገልግሎቱን የሚያገኙበት ማዕከል መሆናቸው በመግለጫው ተመላክቷል።


የከተማዋ የፅዳት አስተዳደር አጄንሲ በበኩሉ የገና በዓል የእርድ በዓል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በከተማዋ ሊሰከት የሚችለውን ቆሻሻ ለማስወገድ የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን የኤጀንሲው ም/ክ ዋና ዳይሬክተር ፃዲክ ሽኩር አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን በበዓላቱ ወቅት የሚፈጠሩ የእሳት እና ተያያዥ ጉዳዮች እንዳይከሰቱ ተጨማሪ የሰው ሀይል በማደራጀት እና አስፈላጊውን ግብአት በሟሟላት ለበዓላቱ መዘጋጀታቸውን ም/ክ ኮሚሽነር ይክፈለው ገ/መስቀል ገልፀዋል።
ተቋማቱ በጋራ በሰጡት መግለጫ ማህበረሰቡ በበዓላት ወቅት የሚፈጠሩ አደጋዎችን ለመከላከልን እና የአከባቢ ብክለትን እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












