አዲስ አበባ | ታህሳስ 23፤ 2016| NBC ETHIOPIA – በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር በሽታ የሚባለው አንዲት ሴት ከዚህ በፊት የስኳር በሽታ የሌለባት ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የስኳር በሽታ እንዳለባት ሲረጋገጥ ነው።

ልክ እንደሌሎች የስኳር በሽታ ዓይነቶች፣ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር በሽታም ህዋሳት (ሴሎች) ስኳር የሚጠቀሙበትን መንገድ ያስተጓጉላል።
መንስኤው ምንድን ነው?

(የእንግዴ ልጅ (Placenta) በማደግ ላይ ላለው ህጻን አልሚ ምግቦች እና ውሃ ይሰጣል በተጨማሪም እርግዝናን ለመጠበቅ የተለያዩ ሆርሞኖችን ያመነጫል። እነዚህ ሆርሞኖች የሰውነቷ ሕዋሳት ኢንሱሊንን በአግባቡ እንዳይጠቀሙ ያደርጓቸዋል፣ እንደወትሮው ለኢንሱሊን መልስ መስጠትም ያቆማሉ። ይህም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን እና የሰውነቷን የኢንሱሊን ፍላጎት ይጨምራል።
በእርግዝና ጊዜ ለሚከሰት የስኳር በሽታ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

* ከእርግዝና በፊት ከመጠን ያለፈ ውፍረት መኖር
* አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ
*ከእርግዝና በፊት የቅድመ የስኳር (prediabetes) በሽታ መኖር
* በቀድሞ እርግዝና ወቅት በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር በሽታ ከነበረ
* የስኳር በሽታ ያለበት የቅርብ የቤተሰብ አባል መኖር
* ከዚህ ቀደም 4 ኪሎግራም (ከ9 ፓውንድ) በላይ የሚመዝን ህፃን ልጅ ከወለደች
ሕክምናው ምንድነው?

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር በሽታ ሕክምና በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን መቆጣጠር እና በማህፀን ውስጥ የሚገኘውን ህፃን እድገትና ጤንነት መከታተል ላይ ያተኩራል።
ጤናማ ምግብን በትክክለኛው ጊዜ መመገብ እና መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቀንሳል። እንዲሁም ሰውነታችን ኢንሱሊንን በአግባቡ እንዲጠቀም ያደርጋል። ጤናማ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የደምን ስኳር መጠን ለመቆጣጠር በቂ ካልሆኑ መድሃኒት ሊጀመር ይችላል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












