አዲስ አበባ | ህዳር 11፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ዛሬ ቀን 10፡00 ይጫዋታል፡፡
በአሜሪካ፣ ካናዳና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት ወደሚሰናዳው የ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ግጥሚያቸውን እያከናወኑ የሚገኙት ዋልያዎቹ ዛሬ ቀን 10፡00 በኤል አብዲ ስታዲየም ከቡርኪና ፋሶ ጋር የሚያደርጉት ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ነው፡፡
ጨዋታውን ጋምቢያዊው የፖሊስ አባል ጃሚህ ለሚን በዋና ዳኝነት ይመሩታል ተብሏል፡፡
ምድብ አንድ ላይ ከሴራሊዮን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ግብጽ፣ ጊኒ ቢሳውና ጅቡቲ ጋር የተደለደሉት ዋልያዎቹ በጭጋግ በተሞላው የአየር ንብረት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሴራሊዮን አቻው ጋር አድርገው ያለ ምንም ግብ በአቻነት ማጠናቀቃቸው አይዘነጋም፡፡
በካዛብላንካ ሞላይ ረሺድ ስታዲየም መደበኛ ልምምዱን ሲያከናወን የነበረው ብሔራዊ ቡድኑ ትናንት የመጨረሻ ልምምድ ማድረጉንና ጨዋታው ወደሚደረግበት ኤል ቺዳድ ከተማ ማምራቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ይጠቁማል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












