አዲስ አበባ | ህዳር 12፤ 2016| NBC ETHIOPIA- ሲሰሩበት ከነበረበት ባር እና ሬስቶራንት ውስጥ ተመሳሳይ ቁልፍ በመጠቀም 324 ሺህ 950 ብር ሰርቀው ሊሰወሩ የሞከሩ ሁለት ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን የፈፀሙት ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 6 ገደማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ጀሌሳ መብራት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የአንድ ግለሰብ ባር እና ሬስቶራንት ውስጥ ሲሆን በጓሮ በኩል ወደ ውስጥ በመዝለቅ እና ገንዘብ የሚቀመጥበትን የቢሮ በር በተመሳሳይ ቁልፍ ከፍተው በመግባት ወንጀሉን ፈፅመው ሊሰወሩ ሲሉ ፖሊስ ባገኘው መረጃ እጅ ከፍንጅ እንደያዛቸው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የላምበረት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ ገልፀዋል፡፡
በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራው መቀጠሉን የተናገሩት ኃላፊው በተለያዩ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፀምባቸው በውሎ ሽያጫቸው የሚያገኙትን ገንዘብ በንግድ ቦታቸው ላይ ትተው ከመሄድ ይልቅ ወደ ባንክ ቢያስገቡ አልያም ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ላይ ቢያስቀምጡ የተሻለ እንደሚሆን መጠቆማቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












