Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Analysis

የኢትዮጵያ የCOP32 ዝግጅትና ዓለምአቀፋዊ የአየር ንብረት ለውጥ አዲስ ምዕራፍ!

የኢትዮጵያ የCOP32 ዝግጅትና አለምአቀፋዊ የአየር ንብረት ለውጥ አዲስ ምዕራፍ!

November 10, 2026
in Analysis
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አመሰራረትና አመጣጥ በድንገት የተከሰተ ሳይሆን፣ የዓለም ሳይንቲስቶች ባደረጉት ረጅም ሂደትና ደረጃ በደረጃ የተገነቡ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን አልፎ የተፈጠረ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ በበርሊን ጀርመን እንደተካሄደ የሚነገረው የcop1 ጉባኤ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ንቁ ተሳትፎ ዛሬም ድርስ እየተከናወነ ይገኛል ።​ምንም እንኳን የሁሉም የCOP ጉባኤዎች አጠቃላይ ግብ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ቢሆንም፣ በየዓመቱ የውይይት መድረኩ በተለያዩ ሀገራት ይካሄዳል።

በቱርክዬ የተካሄደው COP31 በታዳሽ ኃይል መስፋፋት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ መርሀግብር የፋይናንስ አቅርቦት እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት እየተደረገ ይገኛል። በጉባኤውም ከነዳጅ ወደ ታዳሽ ኃይል አጠቃቀም የሚደረገውን ሽግግር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ፤ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ ከተሞችን መገንባት፤ ከበካይ ጋዝ ልቀት ቅነሳ ግቦች ጎን ለጎን ለአጭር ጊዜ ከፍተኛ የሙቀት መጨመር ሂደትን የሚያስከትሉ እንደ ሚቴን ያሉ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር እና የቆሻሻ መጠንን መቀነስ የሚሉ ጉዳዮች ተካተውበታል።

በዚህ ስብሰባ ላይ ታዳጊ ሀገራት የሙቀት አማቂ ጋዞችን በመቀነስ ሂደት የሚያጋጥማቸውን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቶች የተደረጉ ሲሆን፣ ቱርክዬም የራሷን የንጹህ ኃይል አጠቃቀም ተሞክሮ ለዓለም በማካፈል የዓለም አቀፍ ትብብር አስፈላጊነትን አስምራበታለች።

ጉባኤው የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የታቀዱ ግቦችን ከወረቀት ወደ ተግባር ለማሸጋገር ትልቅ መሰረት የጣለ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞትዮስ በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ31ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ላይ የኢትዮጵያን ልዑክ በከፍተኛ ደረጃ እየመሩ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ቀጣዩን የ32ኛውን የ COP ጉባኤ (COP32) በአዲስ አበባ ለማስተናገድ የምታደርገውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችና የሽግግር ሂደት እንዲሁም ተመራጭ መሆኗን በይፋ አስተዋውቀዋል።

​ኢትዮጵያ ቀጣዩን የCOP32 ለማዘጋጀት መመረጧ በአፍሪካ አህጉር ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚጠበቅ አጋጣሚ ሆኗል። አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ማዕከል በመሆኗና አገሪቱም በዘላቂ ልማት ዙሪያ ባላት ቁርጠኝነት የተነሳ፣ ይህንን ግዙፍ አለም አቀፍ ጉባኤ ማስተናገዷ ቀጠናዊ እና አህጉራዊ ተሳትፎዋን ይበልጥ ያጎላዋል።

ኢትዮጵያ ጉባኤውን ለማዘጋጀት የምታደርገው ቅድመ ዝግጅት የዲፕሎማቲክ ተጽዕኖዋን ከመጨመር ባሻገር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂዎቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል ይፈጥርላታል።

​ከዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ዝግጅቶች ጎን ለጎን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ ተወካዮችን፣ የሀገር መሪዎችን እና የአየር ንብረት ባለሙያዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል አስተማማኝ የአደረጃጀት እና የደህንነት ስርዓት በመዘርጋት ላይ ትኩረት ተደርጓል።

ይህ ዝግጅት የኢትዮጵያን የኮንፈረንስ ቱሪዝም (MICE) አቅም ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።​በCOP32 ዝግጅት ወቅት ኢትዮጵያ እንደ “አረንጓዴ አሻራ” ያሉ ሀገር በቀል ፕሮጀክቶችን እና ታዳሽ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ተሞክሮዎቿን እንደ ዋና ማሳያ ታቀርባለች።

ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና የደን ልማት ምን ያህል ወሳኝ እንደሆኑ ኢትዮጵያ ለማሳየት የምትሄድበት ተሞክሮ ትልቅ ማረጋገጫ ይሆናል። ይህም አገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በአረንጓዴ አሻራ ፋይናንስ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያስችላትን እድል ያሰፋላታል።
​
​በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በ COP 32 የምታደርገው ዝግጅት የታዳጊ ሀገራትን ድምፅ በግንባር ቀደምትነት ለማሰማት ትልቅ መድረክ ይሆናል። ኢትዮጵያ ጉባኤውን ስታካሂድ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የራሷን ዘላቂ ጥቅም ከማረጋገጧም በላይ፣ ለአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ጥያቄዎች ጠንካራ መሟገቻ መድረክ በመሆን ታሪካዊ አሻራዋን ታሳርፋለች።

በ- ታደለ ገበየሁ

Tags: COP32EthiopiaGreen Legacy
ShareTweetShare
Previous Post

የአዲስ አበባ የአደባባይ ፕላዛዎች ከታሪካዊ ማዕከላት ባሻገር

Next Post

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዝዳንትና ባርቤዶስ ጥቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

Related Posts

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር
Analysis

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

November 16, 2026
10
“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ
Analysis

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

November 16, 2026
20
ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ
Analysis

ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ

November 14, 2026
57
ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!
Analysis

ሚዲያዎችና ብሄራዊ ጥቅም

November 11, 2026
21
ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!
Analysis

ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!

November 11, 2026
26
የታሪክ፣ የሉዓላዊነትና የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ
Analysis

የታሪክ፣ የሉዓላዊነትና የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ

November 10, 2026
20
Next Post
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዝዳንትና ባርቤዶስ ጥቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዝዳንትና ባርቤዶስ ጥቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!

ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!

ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!

ሚዲያዎችና ብሄራዊ ጥቅም

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?