ኢራን በኑክሌር ዙሪያ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት ጋር ተባባሪ መሆን “ከእንግዲህ አስፈላጊነቱ አይታየኝም” አለች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አውሮፓውያን ከኑክሌር ተቆጣጣሪ ድርጅቱ(አይ ኤ ኢ ኤ) ጋር የሚኖረውን የትብብር አመክንዮ ገደል ከተውታል በሚል አስገንዝበዋል። በኢራን ላይ ምዕራባውያን ዳግም ማዕቀብ እንዲጣል ማድረጋቸው መተማመን እንዳይኖር አድርጓል ሲሉም አራግቺ ወቅሰዋል።
ከድርጅቱ ጋር አብረን ለመስራት የሚያስችል አጋጣሚ እየጠፋ ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአሁን በኋላ የካይሮው ስምምነት ጥቅም የለውም በሚልም በቴህራን ለውጭ አገራት ዲፕሎማቶች አሳውቀዋል።
ኢራን እና የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት በተያዘው መስከረም ስምምነት ላይ መድረሰቻው አይዘነጋም።
እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ ቴህራን ከአይ ኤ ኢ ኤ ጋር የነበራትን ግንኙነት በማቋረጧ የመንግስታቱ ድርጅት ዳግም ለፍተሻ እና ግምገማ ዕድሉን ለማግኘት ብዙ ጥረት አድርጎ ስምምነት ላይም መድረስ ችሎ ነበር።
በተለይም ጀርመን ፣ፈረንሳይ እና ብሪታንያ (ኢ3) በኢራን ላይ ዳግም ጫና መፍጠራቸው ለአያቶላዎቹ የሚዋጥ ሆኖ አልተገኘም። ሁሉም የ2015ቱ የኑክሌር ስምምነቱ ፈራሚ አገራት የመንግስታቱ ድርጅት በኢራን ላይ ዳግም ማዕቀብ እንዲጥል ነገሮችን አመቻችተዋል በሚል አያቶላዎቹ ይከሳሉ።
ኢራን ዓለም አቀፍ የኑክሌር ስምምነትን ጥሳለች በሚል ምዕራቡ ዓለም ጫና መፍጠሩ ቴህራንን ተባባሪ እንዳትሆን አድርጓታል የሚል መረጃም ተጋርቷል ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












