የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዋሽንግተን ቶምሃዋክ ሚሳኤል ለዩክሬን የምትሰጥ ከሆነ፣ የአሜሪካ እና ሩሲያ ግንኙነት ያበቃለታል አሉ።
አሜሪካ ይሄን ካደረገች በሞስኮ እና ዋሽንግተን መካከል ተፈጥሮ የነበረው አወንታዊ መንፈስ መፍረሱ አይቀሬ ነው ብለዋል ፑቲን። ቶምሃዋክ ሚሳኤል ለዩክሬን መስጠት አሜሪካ በጦርነቱ እንደተሳተፈች እቆጥረዋለሁ ያሉት ፑቲን፣ አዲስ ውጥረት ከመፍጠር ውጭ የሚመጣ ለውጥ የለም ሲሉ ነው ያስጠነቀቁት።
ሩሲያ ለየትኛውም ጥቃት ምላሽ እንደምትሰጥ ከክሬምሊን የሚወጡ መግለጫዎችም እያመለከቱ ነው። ዘለንስኪ ቶምሃዋክ ሚሳኤል እንዲሰጣቸው በተጋጋሚ ትራምፕን ቢወተውቱም እስካሁን መልስ አላገኙም።
ቶምሃዋክ ሚሳኤል እስከ 2500 ኪሜ ድረስ መምዘግዘግ የሚችል እንደሆነ ወታደራዊ ተንታኞች ይናገራሉ ።
አናዶሉ እንደዘገበው
በ-ቶማይ መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












