በ”ህብረት ችለናል” በሚል መሪ ሀሳብ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በሲዳማ ክልል ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።
ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ከክልሉ የተለያዩ አካበቢዎች ወደ ሀዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ የተመሙ ነዋሪዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የተሰማቸውን ደስታ በዜማና ቤሎች መርሃ ግብሮች እየገለጹ ይገኛሉ።
ሰልፈኞቹ “ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የብልፅግናችን ምልክት ነው” ፣ “በህብረት ችለናል” ፣ “ግድቡን በስኬት ማጠናቀቅ የድል ሽልማታችን ነው” ፣ “ግድባችን የህብረብሔራዊነታችንና የአንድነታችን መሠረት ነው” ፣ “የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት ነው” የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።
የድጋፍ ሰልፉ የክልሉ ርዕሰ መተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው ሲል ኢዜአ ዘግቦታል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












